አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው።
ዘሌዋውያን 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከላሞች መንጋ መካከል የሚቀርብ ከሆነ፣ ነቀፋ የሌለበትን ተባዕቱን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያቅርበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል። |
አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው።
“የምትወድደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ከፍተኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
ጉባኤውም ያመጡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቍጥር ሰባ ወይፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደ ክፍላቸው ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ።
የእስራኤልንም ልጆች ጐልማሶች ላከ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም አቀረቡ፤ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን ሠዉ።
አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።
በዚያ እናገርህ ዘንድ ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘወትር መሥዋዕት ይሆናል።
አሮንም በነጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ሠዋ፤ የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረበ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ።
ከእነርሱም ሰው ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ እንዳነሣሣው፥ መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለምስክሩ ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለመቅደስ ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ።
ከእስራኤል ልጆችም ያመጡ ዘንድ ልባቸው ያስነሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጦታ በፈቃዳቸው አመጡ።
ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገንዘቡ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር ያምጣ፤ ወርቅና ብር፥ ናስም፤
እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።
ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበረ።
“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤአለሁ፤ የበሬና የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።
“በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው ለዘለዓለም ይገዙልኛል፤ በዚያም እቀበላችኋለሁ፤ በዚያም ቀዳምያታችሁን፥ በኵራታችሁንም፥ የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እጐበኛለሁ።
የሚቃጠለውንም መሥዋዕት፥ የኀጢአቱንና የበደሉንም መሥዋዕት ያርዱባቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።
“ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መባ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን ተባቱን፥ የፊት እግሮቹንና ራሱን ጨምሮ ያቀርበዋል።
“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የተመረጠ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ወይም የድኅነት መሥዋዕት ያደርገው ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ በሌላም ቦታ ቢያርደው፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአልና፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
ለእነርሱ እንዲህ በላቸው፥ “ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥
ነዶውንም ባቀረባችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
ከኅብስቱም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ጠቦቶች፥ ከመንጋውም አንድ ወይፈን፥ ሁለትም ነውር የሌለባቸው አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት እንዲሆን መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸው፥ ወይናቸውም ለእግዚአብሔር ይሁን።
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
የማኅበሩም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑንም በእግዚአብሔር ፊት ያርዱታል።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
ነውር የሌለበትን በሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣዋል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
“ሰው ኀጢአትን ቢሠራ፥ የእግዚአብሔርንም ትእዛዝ ቸል ቢል፥ ያኖረበትን አደራ ወይም የኅብረትን ገንዘብ ወስዶ ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥
የቍርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱ በሚቀርብበት ቀን ይብሉት፤ ከእርሱም የቀረውን በነጋው ይብሉት፤
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።
ሙሴም አሮንን አለው፥ “ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እንቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።
በፈቃዳችሁም ቢሆን በበዓላችሁም ቢሆን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእለቱን አብዝታችሁ በአመጣችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
ለሚቃጠልም መሥዋዕት፥ ወይም ለሌላ መሥዋዕት፥ ወይም ስእለትን ለመፈጸም፥ ወይም ለደኅንነት መሥዋዕት ከላም ወገን ለእግዚአብሔር ብታዘጋጅ፥
“እግዚአብሔር ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው፤ መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር ያመጡልህ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
ባላቅም በለዓምን አለው፥ “ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድድ ይሆናል።”
በለዓምም ባላቅን፥ “በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግዚአብሔር ቢገለጥልኝ፥ ቢገናኘኝም እሄዳለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ቃል እነግርሃለሁ” አለው። ባላቅም በመሠዊያው ዘንድ ቆመ፤ በለዓም ግን እግዚአብሔርን ይጠይቅ ዘንድ አቅንቶ ሄደ።
“በወሩም መባቻ ለእግዚአሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥
በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ።
በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ሌላ እነርሱንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ታቀርባላችሁ፤ ነውርም የሌለባቸው ይሁኑ።
ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ከላሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦቶች፥
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኵሰት እንዳያገኝባት፥ ቤተ ክርስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ፤
ሥጋውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የመሥዋዕትህም ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብላው።
“በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?