Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘሌዋውያን 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቢኖር መባ​ች​ሁን ከእ​ን​ስሳ ወገን ከላ​ሞች ወይም ከበ​ጎች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

3 “መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።

4 ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።

5 በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።

6 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይገ​ፍ​ፈ​ዋል፤ በየ​ብ​ል​ቱም ይቈ​ር​ጠ​ዋል።

7 የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጆች በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ በእ​ሳ​ቱም ላይ ዕን​ጨት ይረ​በ​ር​ባሉ፤

8 የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የተ​ቈ​ረ​ጡ​ትን ብል​ቶች፥ ራሱ​ንም፥ ስቡ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ይረ​በ​ር​ቡ​ታል።

9 የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።

10 “ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።

11 በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።

12 በየ​ብ​ል​ቱም ራሱን፥ ስቡ​ንም ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ካህ​ና​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ይረ​በ​ር​ቡ​ታል፤

13 የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።

14 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከዎ​ፎች ቢሆን፥ ቍር​ባ​ኑን ከዋ​ኖስ ወይም ከር​ግብ ያቀ​ር​ባል።

15 ካህ​ኑም ወደ መሠ​ዊ​ያው ያቀ​ር​በ​ዋል፤ አን​ገ​ቱ​ንም ይቈ​ር​ጠ​ዋል፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያኖ​ረ​ዋል። ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያን​ጠ​ፈ​ጥ​ፈ​ዋል፤

16 የሆድ ዕቃ​ው​ንም ከላ​ባ​ዎች ጋር ለይቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል በአ​መዱ ስፍራ ይጥ​ለ​ዋል፤

17 ከክ​ን​ፎ​ቹም ይሰ​ብ​ረ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ለ​የ​ውም። ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያኖ​ረ​ዋል፤ መሥ​ዋ​ዕቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos