Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 29:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በው​ኃም ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም አሮንና ወንድ ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በማምጣት በውሃ ዕጠባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አሮንና ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “አሮንንና ልጆቹን እኔ ወደምመለክበት ድንኳን ደጃፍ አምጥተህ በውሃ እንዲታጠቡ ንገራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 29:4
18 Referencias Cruzadas  

አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አቅ​ር​በህ በውኃ ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


በውኃ ጥም​ቀ​ትና በቃሉ ይቀ​ድ​ሳ​ትና ያነ​ጻት ዘንድ፥


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


በመ​ሸም ጊዜ ሰው​ነ​ቱን በውኃ ይታ​ጠብ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመ​ለስ።


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በድ​ን​ኳኑ ደጅ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ዘረጋ።


ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።


በአ​ንድ መሶ​ብም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑና ከሁ​ለቱ አውራ በጎች ጋር በመ​ሶብ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቅ​ርብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሰብ​ስብ።


ካህ​ና​ቱም በገቡ ጊዜ ከመ​ቅ​ደሱ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አይ​ወ​ጡም፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖ​ሩ​ታል፤ ሌላም ልብስ ለብ​ሰው ወደ ሕዝብ ይወ​ጣሉ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቀ​ረቡ ጊዜ ይታ​ጠቡ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios