ዘፍጥረት 22:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 አብርሃም ቀና ብሎ ተመለከተ፤ በቍጥቋጦ መካከልም ቀንዶቹ የተጠላለፉ አንድ አውራ በግ ከበስተኋላው አየ፤ ወደዚያው ሄዶ በጉን አመጣና የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አብርሃምም ዓይኑን አንስቶ ሲመለከት፥ ከኋላው እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዛፍ ቊጥቋጦ ተይዞ አየ፥ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና፥ በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 አብርሃም ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ ቀንዶቹ በቊጥቋጦ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር አዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፦ በልጁም ፋንታ መሥውዕት አድርጎ ሠዋው። Ver Capítulo |