Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘኍል 19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በሐ​መደ ዕጐ​ልት የሚ​ፈ​ጸም የኀ​ጢ​አት ስር​የት ሥር​ዐት

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦

2 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው የሕጉ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ መል​ካ​ሚ​ቱን፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ቀይ ጊደር ያመ​ጡ​ልህ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው።

3 እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።

4 አል​ዓ​ዛ​ርም ከደ​ምዋ በጣቱ ይወ​ስ​ዳል፤ ከደ​ም​ዋም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል።

5 ጊደ​ሪ​ቱ​ንም በፊቱ ያቃ​ጥ​ሏ​ታል፤ ቍር​በ​ቷ​ንም፥ ሥጋ​ዋ​ንም፥ ደም​ዋ​ንም፥ ፈር​ስ​ዋ​ንም ያቃ​ጥ​ሉት።

6 ካህ​ኑም የዝ​ግባ ዕን​ጨት ሂሶ​ጵም፥ ቀይ ግም​ጃም ወስዶ ጊደ​ሪቱ በም​ት​ቃ​ጠ​ል​በት እሳት መካ​ከል ይጥ​ለ​ዋል።

7 ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።

8 ያቃ​ጠ​ላ​ትም ሰው ልብ​ሱን በውሃ ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።

9 ንጹ​ሕም ሰው የጊ​ደ​ሪ​ቱን አመድ ያከ​ማ​ቻል፤ ከሰ​ፈ​ሩም ውጭ በን​ጹሕ ስፍራ ያኖ​ረ​ዋል፤ ርኵ​ሰት ለሚ​ያ​ነጻ ውኃ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ይጠ​በ​ቃል፤ ይነ​ጹ​በ​ታ​ልና።

10 የጊ​ደ​ሪ​ቱ​ንም አመድ ያከ​ማ​ቸው ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።


በድን የሚ​ነካ ስለ​ሚ​ነ​ጻ​በት ሕግ

11 “የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።

12 እን​ደ​ዚሁ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ያነ​ጻል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ ንጹሕ አይ​ሆ​ንም።

13 የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የነካ ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ያረ​ክ​ሳል፤ ያ ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ይሆ​ናል፤ ርኵ​ሰቱ ገና በእ​ርሱ ላይ ነው።

14 “ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚ​ገባ ሁሉ በቤ​ቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።

15 መክ​ደ​ኛው ያል​ታ​ሰረ የተ​ከ​ፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።

16 በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።

17 ለአ​ን​ጽሖ እን​ድ​ት​ሆን ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ችው ጊደር አመድ ለር​ኩሱ ይወ​ስ​ዱ​ለ​ታል፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ የም​ንጭ ውኃ ይቀ​ላ​ቅ​ሉ​በ​ታል።

18 ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።

19 ንጹ​ሑም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀንና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በር​ኩሱ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ጻል፤ እር​ሱም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

20 “ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለ​መ​ና​ው​ንም ባያ​ነጻ፥ ያ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አር​ክ​ሶ​አ​ልና ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ነው።

21 ይህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውን ውኃ የሚ​ረጭ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ው​ንም ውኃ የሚ​ነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።

22 ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos