Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለእ​ነ​ርሱ እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት ቢያ​ቀ​ርብ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ቤት በመካከላቸውም ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በማኅበሩ መካከል የሚኖር መጻተኛ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ቤት በመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 17:8
16 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።


“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የተ​መ​ረጠ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገው ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ በሌ​ላም ቦታ ቢያ​ር​ደው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ባያ​መ​ጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈ​ጠ​ር​በ​ታል፤ ደም አፍ​ስ​ሶ​አ​ልና፤ ያም ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ለቍ​ር​ባኑ የበግ ጠቦ​ትን ቢያ​ቀ​ርብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር ዳርቻ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ ባለው በገ​ለ​ዓድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባሉ​በት ወገን፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ መሠ​ዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ሁሉ የሚ​ለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠ​ዊ​ያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ ትክ​ዱት ዘንድ ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀጢ​አት ምን​ድን ነው?


በዚ​ያም ተራራ አናት ላይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አሳ​ም​ረህ ሥራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዉ​ንም በሬ ውሰድ፤ በዚ​ያም በቈ​ረ​ጥ​ኸው በማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸዱ እን​ጨት ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርብ” አለው።


በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ከሕ​ዝቡ ጋር አቀ​ረ​በው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ስለ እስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos