ዘኍል 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በፈቃዳችሁም ቢሆን በበዓላችሁም ቢሆን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእለቱን አብዝታችሁ በአመጣችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ስእለታችሁን ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማድረግ ወይም በበዓላታችሁ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ከላም ወይም ከበግ መንጋ በእሳት ለእግዚአብሔር ስታቀርቡ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስእለታችሁን ለመፈጸም፥ ወይም በፈቃዳችሁ፥ ወይም በበዓላችሁ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ብታቀርቡ፥ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ስለ ስእለት መፈጸም ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በበጎ ፈቃድ ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በተለመዱት የሃይማኖት በዓላት ላይ ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደዚህ ያለውም የምግብ ቊርባን መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ስእለታችሁን ልትፈጽሙ፥ ወይም በፈቃዳችሁ፥ ወይም በበዓላችሁ፥ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ ታደርጉ ዘንድ ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ብታቀርቡ፥ Ver Capítulo |