Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 32:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሮ​ንም በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዋ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ ሕዝ​ቡም ሊበ​ሉና ሊጠጡ ተቀ​መጡ፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በማግስቱም ሕዝቡ በማለዳ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፤ የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚህም በኋላ ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በማግስቱ ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በማግስቱ ሰዎቹ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ተቀምጠው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በነጋውም ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የደኅነትም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:6
10 Referencias Cruzadas  

አሮ​ንም በአ​የው ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን በፊቱ ሠራ፤ አሮ​ንም፥ “ነገ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።


ሕዝ​ቡ​ንም ወደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ጠሩ፤ ሕዝ​ቡም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በሉ፤ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውም ሰገዱ።


“አሕ​ዛብ ተቀ​መጡ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም ጀመር፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ አመ​ለኩ ጣዖ​ትን የም​ታ​መ​ልኩ አት​ሁኑ።


እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos