Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 12:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሥጋ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ርብ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህም ደም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይፍ​ሰስ፥ ሥጋ​ው​ንም ብላው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፣ ሥጋውንም ደሙንም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንም ደሙንም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን፥ ማለትም ሥጋውንና ደሙን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የሌሎች መሥዋዕቶችህ ደም ከአምላክህ ከእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን ልትበላ ትችላለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የሚቃጠለውንም መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንና ደሙን፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የመሥዋዕትህም ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብላው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 12:27
7 Referencias Cruzadas  

የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከቍ​ር​ባ​ና​ችሁ ጋር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን ጨምሩ፤ ሥጋ​ው​ንም ብሉ።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕ​ይ​ወቱ የተ​ነሣ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእ​ና​ንተ ሰጠ​ሁት።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ቢሆን፥ ከላ​ሞች መንጋ ተባት ወይም እን​ስት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ርብ።


ካህ​ኑም ከደ​ምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos