Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘፍጥረት 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የማየ አይኅ መጕ​ደል

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤

2 የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤

3 ውኃ​ውም ከም​ድር ላይ እያ​ደር እየ​ቀ​ለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ።

4 መር​ከ​ቢ​ቱም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን በአ​ራ​ራት ተራ​ሮች ላይ ተቀ​መ​ጠች።

5 ውኃ​ውም እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ወር ድረስ ይጐ​ድል ነበር፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ራ​ሮቹ ራሶች ተገ​ለጡ።

6 ከአ​ርባ ቀን በኋ​ላም ኖኅ የሠ​ራ​ውን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን መስ​ኮት ከፈተ፤

7 ከም​ድ​ርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እን​ደ​ሆነ ያይ ዘንድ ቁራ​ውን ላከው፤ እር​ሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከም​ድር ላይ እስ​ኪ​ደ​ርቅ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሰም።

8 ርግ​ብ​ንም ውኃው ከም​ድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እን​ድ​ታይ ከእ​ርሱ በኋላ ላካት።

9 ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት።

10 ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን እን​ደ​ገና ከመ​ር​ከብ ላካት።

11 ርግ​ብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ በአ​ፍ​ዋም እነሆ፥ የለ​መ​ለመ የወ​ይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከም​ድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ።

12 ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።

13 በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስት መቶ አንድ ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ውኃው ከም​ድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠ​ራ​ትን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን ክዳን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ውኃው ከም​ድር ፊት እንደ ደረቀ አየ።

14 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ምድር ደረ​ቀች።

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፤

16 “አንተ ሚስ​ት​ህ​ንና ልጆ​ች​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ከመ​ር​ከብ ውጣ።

17 ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።”

18 ኖኅም ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንና የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ይዞ ወጣ፤

19 አራ​ዊት ሁሉ፥ እን​ስ​ሳም ሁሉ፥ ወፎ​ችም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከመ​ር​ከብ ወጡ።


ኖኅ መሥ​ዋ​ዕት እንደ አቀ​ረበ

20 ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ።

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።

22 በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos