Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሉቃስ 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ወን​ጌ​ልን ስለ መጻፍ

1 በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው።

2 ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤

3 የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ።

4 የተ​ማ​ር​ኸ​ውን የነ​ገ​ሩን እው​ነት ጠን​ቅ​ቀህ ታውቅ ዘንድ።


ስለ ዘካ​ር​ያ​ስና ስለ ኤል​ሳ​ቤጥ

5 በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ።

6 ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።

7 ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።

8 እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በተ​ራው የክ​ህ​ነ​ትን ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት ጊዜ፥

9 ካህ​ናት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜ ደረሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም ገባ።

10 ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር።

11 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በዕ​ጣን መሠ​ው​ያው በስ​ተ​ቀኝ ቆሞ ታየው።

12 ዘካ​ር​ያ​ስም ባየው ጊዜ ደነ​ገጠ፤ ፍር​ሀ​ትም ረዓ​ድም ወረ​ደ​በት።

13 መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ።

14 ደስ​ታና ሐሤ​ትም ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በመ​ወ​ለ​ዱም ብዙ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

15 እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።

16 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ​ዎ​ችን ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል።

17 እር​ሱም የአ​ባ​ቶ​ችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከ​ሓ​ድ​ያ​ን​ንም ዐሳብ ወደ ጻድ​ቃን ዕው​ቀት ይመ​ልስ ዘንድ፥ ሕዝ​ብ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ዘ​ጋጀ ያደ​ርግ ዘንድ በኤ​ል​ያስ መን​ፈ​ስና ኀይል በፊቱ ይሄ​ዳል።”

18 ዘካ​ር​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዲህ አለው፥ “ይህ እን​ደ​ሚ​ሆን በምን አው​ቃ​ለሁ? እነሆ፥ እኔ አር​ጅ​ች​አ​ለሁ፤ የሚ​ስ​ቴም ዘመ​ንዋ አል​ፏል።”

19 መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ቆ​መው ገብ​ር​ኤል ነኝ፤ ይህ​ንም እነ​ግ​ር​ህና አበ​ሥ​ርህ ዘንድ ወደ አንተ ተል​ኬ​አ​ለሁ።

20 አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።”

21 ሕዝቡ ግን ዘካ​ር​ያ​ስን ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ዘግ​ይቶ ነበ​ርና እጅግ ተደ​ነቁ።

22 ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነ​ር​ሱን ማነ​ጋ​ገር ተሳ​ነው፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት እን​ዳለ ዐወቁ፤ እን​ዲ​ሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸው ኖረ።

23 ከዚ​ህም በኋላ የማ​ገ​ል​ገሉ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ።

24 ከእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች በኋላ ሚስቱ ኤል​ሳ​ቤጥ ፀነ​ሰች፤ ፅን​ስ​ዋ​ንም ለአ​ም​ስት ወር ሸሸ​ገች፤ እን​ዲህ ስትል፦

25 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድ​ቤን ያርቅ ዘንድ በጐ​በ​ኘኝ ጊዜ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ።”


ቅዱስ ገብ​ር​ኤል እመ​ቤ​ታ​ች​ንን እንደ አበ​ሠ​ራት

26 በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መል​አኩ ገብ​ር​ኤል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ስሟ ናዝ​ሬት ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ አን​ዲት የገ​ሊላ ከተማ ከዳ​ዊት ወገን ለሚ​ሆን ዮሴፍ ለሚ​ባል ሰው ወደ ታጨ​ችው ወደ አን​ዲት ድን​ግል ተላከ፤

27 የዚ​ያ​ችም ድን​ግል ስምዋ ማር​ያም ይባል ነበረ።

28 መል​አ​ኩም ወደ እር​ስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥ ጸጋ​ንም የተ​መ​ላሽ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ” አላት።

29 እር​ስ​ዋም በአ​የ​ችው ጊዜ ከአ​ነ​ጋ​ገሩ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠ​ችና “ይህ እን​ዴት ያለ ሰላ​ምታ ነው?” ብላ ዐሰ​በች።

30 መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላት፥ “ማር​ያም ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ተ​ሻ​ልና አት​ፍሪ።

31 እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ኢየ​ሱስ ትይ​ዋ​ለሽ።

32 እር​ሱም ታላቅ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ዙፋን ይሰ​ጠ​ዋል።

33 ለያ​ዕ​ቆብ ወገ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ይነ​ግ​ሣል፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ፍጻሜ የለ​ውም።”

34 ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “ወንድ ስለ​ማ​ላ​ውቅ ይህ እን​ዴት ይሆ​ን​ል​ኛል?” አለ​ችው።

35 መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።

36 እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።

37 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር የለ​ምና”።

38 ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “እነ​ሆኝ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያው አለሁ፤ እንደ ቃልህ ይሁ​ን​ልኝ” አለ​ችው፤ ከዚህ በኋ​ላም መል​አኩ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ሄደ።


ማር​ያም ወደ ኤል​ሣ​ቤጥ ስለ መሄ​ድዋ

39 በዚ​ያም ወራት ማር​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተ​ማም ደረ​ሰች።

40 ወደ ዘካ​ር​ያስ ቤትም ገብታ ለኤ​ል​ሣ​ቤጥ ሰላ​ምታ ሰጠ​ቻት።

41 ኤል​ሳ​ቤ​ጥም የማ​ር​ያ​ምን ሰላ​ምታ በሰ​ማች ጊዜ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ዘለለ፤ በኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባት።

42 በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው።

43 የጌ​ታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ?

44 እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና።

45 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የነ​ገ​ሩሽ ቃል እን​ደ​ሚ​ሆን የም​ታ​ምኚ አንቺ ብፅ​ዕት ነሽ።”

46 ማር​ያ​ምም እን​ዲህ አለች፥ “ሰው​ነቴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታከ​ብ​ረ​ዋ​ለች።

47 ልቡ​ና​ዬም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች።

48 የባ​ር​ያ​ውን ትሕ​ትና ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትው​ልድ ሁሉ ብፅ​ዕት ይሉ​ኛል።

49 ታላቅ ሥራን ሠር​ቶ​ል​ኛ​ልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።

50 ይቅ​ር​ታ​ውም ለሚ​ፈ​ሩት ለልጅ ልጅ ነው።

51 በክ​ንዱ ኀይ​ልን አደ​ረገ፤ በል​ባ​ቸው ዐሳብ የሚ​ታ​በ​ዩ​ት​ንም በተ​ና​ቸው።

52 ኀያ​ላ​ኑን ከዙ​ፋ​ና​ቸው አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ትሑ​ታ​ኑ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው።

53 የተ​ራ​ቡ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ ባለ​ጠ​ጎ​ች​ንም ባዶ እጃ​ቸ​ውን ሰደ​ዳ​ቸው።

54 ብላ​ቴ​ና​ውን እስ​ራ​ኤ​ልን ተቀ​በ​ለው፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንም ዐሰበ።

55 ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እንደ ተና​ገ​ረው።”

56 ማር​ያ​ምም ሦስት ወር ያህል በእ​ር​ስዋ ዘንድ ተቀ​መ​ጠች፤ ከዚህ በኋ​ላም ወደ ቤቷ ተመ​ለ​ሰች።


ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ልደት

57 የኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም የመ​ው​ለ​ጃዋ ጊዜ ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች።

58 ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።

59 ከዚ​ህም በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት መጡ፤ በአ​ባ​ቱም ስም ዘካ​ር​ያስ ብለው ጠሩት።

60 እናቱ ግን መልሳ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ዮሐ​ንስ ይባል እንጂ” አለች።

61 እነ​ር​ሱም፥ “ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ስሙ እን​ደ​ዚህ የሚ​ባል የለም” አሉ​አት።

62 አባ​ቱ​ንም ጠቅ​ሰው፥ “ማን ሊሉት ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት።

63 ብራ​ናም ለመ​ነና “ስሙ ዮሐ​ንስ ይባል” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም አደ​ነቁ።

64 ያን​ጊ​ዜም አፉ ተከ​ፈተ፤ አን​ደ​በ​ቱም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ።

65 በዚ​ያም ሀገር ሰው ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ሆነ፤ ይህም ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሁሉ ተወራ።

66 የሰ​ሙ​ትም ሁሉ፥ “እን​ግ​ዲህ ይህ ሕፃን ምን ይሆን?” እያሉ በል​ባ​ቸው አኖ​ሩት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና።

67 በአ​ባቱ በዘ​ካ​ር​ያ​ስም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​በት፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ትን​ቢት ተና​ገረ፦

68 “ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤

69 ከባ​ር​ያው ከዳ​ዊት ቤት የም​ን​ድ​ን​በ​ትን ቀንድ አስ​ነ​ሣ​ልን፤

70 ከጥ​ንት ጀምሮ በነ​በሩ በቅ​ዱ​ሳን በነ​ቢ​ያት አፍ እንደ ተና​ገረ።

71 ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ንም ሁሉ እጅ ያድ​ነን ዘንድ።

72 ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ።

73 ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ውን መሐላ ያስብ ዘንድ።

74 ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ድነን ያለ ፍር​ሀት፥

75 በቅ​ድ​ስ​ናና በጽ​ድቅ በፊቱ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ እን​ድ​ና​መ​ል​ከው ይሰ​ጠን ዘንድ።

76 አን​ተም ሕፃን፥ የል​ዑል ነቢይ ትባ​ላ​ለህ፤ መን​ገ​ዱን ትጠ​ርግ ዘንድ በፊቱ ትሄ​ዳ​ለ​ህና።

77 ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ውቁ ለአ​ሕ​ዛብ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።

78 ከአ​ር​ያም በጐ​በ​ኘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በቸ​ር​ነቱ።

79 በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”

80 ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos