በዚያም አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና፤
ዘፍጥረት 49:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣ እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤ ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፥ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ብርቱ በሆነ በያዕቆብ አምላክ ኀይል፥ በእስራኤል እረኛና ጠባቂ ብርታት፥ የእርሱ ቀስት ጽኑ ይሆናል፤ ክንዱም ይበረታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ |
በዚያም አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና፤
ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ፥ ለአባቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእያንዳንዱ ሰው እየሰፈረ እህልን ለምግብ ይሰጣቸው ነበር።
ያዕቆብም ባረካቸው፤ እንዲህም አለ፥ “አባቶች አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ ደስ ያሰኙት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
አሁንም አትፍሩ፤ እኔ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም፤ በልባቸው የሚገባ ነገርም ነገራቸው።
አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
የእስራኤልንም ንጉሥ አለው፥ “እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን።” ዮአስም እጁን በቀስቱ ላይ ጫነ፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ለእስራኤል ኀያላን ወዮላቸው! በጠላቶች ላይ ቍጣዬ አይበርድም፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፤ የሚያጕረመርሙም መታዘዝን ይማራሉ፤ ዲዳ አንደበትም ሰላም መናገርን ይማራል።”
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
የአስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን ይበላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኀኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብን ኀይል የምደግፍ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፤ የነገሥታትንም ብልጽግና ትበያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ፥ መድኀኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፣ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፣ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?
‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”
ጌታችን ኢየሱስም ተመለከተና እንዲህ አላቸው፤ “ግንበኞች የናቁአት ድንጋይ እርስዋ የማዕዘን ራስ ሆነች፥ የሚለው ጽሑፍ ምንድነው?
እንግዲህ የሌላውን ሎሌ የምትነቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለጌታው ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያነሣው ይችላልና ይቆማል።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።
ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
ነገር ግን ተራራማው ሀገር ለእናንተ ይሆናል፤ ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩታላችሁ፤ ለእናንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የተመረጡ ፈረሶችና የብረት ሰረገሎች ቢሆኑላቸው፥ የበረቱ ቢሆኑም እናንተ እስክታጠፉአቸው ድረስ ትበረቱባቸዋላችሁ” አላቸው።