Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘፍጥረት 49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ያዕ​ቆብ ልጆ​ቹን እንደ መረ​ቃ​ቸው

1 ያዕ​ቆ​ብም ልጆ​ቹን ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሚ​ያ​ገ​ኛ​ች​ሁን እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ።

2 እና​ንት የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ስሙም፤ አባ​ታ​ችሁ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አድ​ምጡ።

3 “ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።

4 እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።

5 “ስም​ዖ​ንና ሌዊ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናቸው፤ በጭ​ቅ​ጭ​ቃ​ቸ​ውና በጦ​ራ​ቸው ዐመ​ፅን ፈጸ​ሙ​አት።

6 በም​ክ​ራ​ቸው ሰው​ነቴ አት​ገ​ና​ኛ​ቸው፤ ዐሳ​ቤም በአ​መ​ፃ​ቸው አት​ተ​ባ​በ​ርም፤ በቍ​ጣ​ቸው ሰውን ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ በገዛ ፈቃ​ዳ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ርን ሥር ቈር​ጠ​ዋ​ልና።

7 ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።

8 “ይሁዳ፥ ወን​ድ​ሞ​ችህ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ እጅህ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ደን​ደስ ላይ ነው፤ የአ​ባ​ትህ ልጆች በፊ​ትህ ይሰ​ግ​ዳሉ።

9 ይሁዳ የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ ወጣህ፤ እንደ አን​በሳ ተኛህ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ህም፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦል የሚ​ቀ​ሰ​ቅ​ስህ የለም።

10 መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤

11 አህ​ያ​ይ​ቱን በወ​ይን ግንድ ያስ​ራል፤ የአ​ህ​ያ​ይ​ቱ​ንም ግል​ገል በወ​ይን ሐረግ፤ ልብ​ሱን በወ​ይን ያጥ​ባል፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም በዘ​ለ​ላው ደም።

12 ዐይ​ኖቹ ከወ​ይን ይልቅ ደስ ያሰ​ኛሉ፤ ጥር​ሱም ከወ​ተት ይልቅ ነጭ ነው።

13 “ዛብ​ሎን ጫማ​ውን አዝቦ ይኖ​ራል፤ እር​ሱም እንደ መር​ከ​ቦች ወደብ ይሆ​ናል፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ሲዶና ይሰ​ፋል።

14 “ይሳ​ኮር መል​ካም ነገ​ርን ወደደ፤ በተ​ወ​ራ​ራ​ሾ​ቹም መካ​ከል ያር​ፋል።

15 ዕረ​ፍ​ትም መል​ካም መሆ​ን​ዋን፥ ምድ​ሪ​ቱም የለ​ማች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ምድ​ርን ያር​ሳት ዘንድ ትከ​ሻ​ውን ዝቅ አደ​ረገ፤ በሥ​ራም ገበሬ ሆነ።

16 “ዳን ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ እንደ አንዱ በወ​ገኑ ይፈ​ር​ዳል፤

17 ዳን በጎ​ዳና ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ደባ እባብ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዱም የፈ​ረ​ሱን ሰኰና እን​ደ​ሚ​ና​ደፍ እንደ ቀን​ዳም እባብ ነው፤ ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ወደ​ኋ​ላው ይወ​ድ​ቃል።

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያድ​ነው ዘንድ ይጠ​ብ​ቃል።

19 “ጋድን ሽፍ​ቶች ቀሙት፤ እር​ሱም ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ታ​ትሎ ቀማ​ቸው።

20 “የአ​ሴር እን​ጀራ ወፍ​ራም ነው፤ እር​ሱም ለአ​ለ​ቆች ደስ የሚ​ያ​ሰኝ መብ​ልን ይሰ​ጣል።

21 “ንፍ​ታ​ሌም በፍ​ሬው ላይ ውበ​ትን የሚ​ሰጥ ሰፊ ዘን​ባባ ነው።

22 “ዮሴፍ የሚ​ያ​ድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተ​ወ​ደደ የሚ​ቀ​ና​ል​ኝና የሚ​ያ​ድ​ግ​ልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ለ​ስም ጐል​ማሳ ነው።

23 በም​ክ​ራ​ቸው የሰ​ደ​ቡት ጌቶች ሆኑ​በት፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ወጉት፤

24 ነገር ግን ቀስ​ቶ​ቻ​ቸው በኀ​ይል ተቀ​ጠ​ቀጡ፤ የእ​ጆ​ቻ​ቸው ክንድ ሥርም በያ​ዕ​ቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚ​ያም በአ​ባ​ትህ አም​ላክ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን አጸ​ናው።

25 “የእኔ አም​ላክ ረዳህ፤ ከላይ በሰ​ማይ በረ​ከት፥ ሁሉ በሚ​ገ​ኝ​ባት፥ በም​ድር በረ​ከት፥ በጡ​ትና በማ​ኅ​ፀን በረ​ከት ባረ​ከህ፤

26 የአ​ባ​ት​ህና የእ​ና​ትህ በረ​ከ​ቶች ጽኑ​ዓን ከሆኑ ከተ​ራ​ሮች በረ​ከ​ቶች ይልቅ ይበ​ል​ጣሉ፤ ዘለ​ዓ​ለ​ማ​ው​ያን ከሆኑ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በረ​ከ​ቶች ይልቅ ኀያ​ላን ናቸው፤ እነ​ር​ሱም በዮ​ሴፍ ራስ ላይ ይሆ​ናሉ፤ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አለቃ በሆ​ነ​ውም ራስ አናት ላይ ይሆ​ናሉ።

27 “ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”

28 እነ​ዚ​ህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ናቸው፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ይህን ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ው​ንም እንደ በረ​ከ​ታ​ቸው ባረ​ካ​ቸው።


የያ​ዕ​ቆብ መሞ​ትና መቀ​በር

29 እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥

30 አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።

31 አብ​ር​ሃ​ም​ንና ሚስቱ ሣራ​ንም በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንና ሚስቱ ርብ​ቃ​ንም በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም እኔ ልያን ቀበ​ር​ኋት

32 እር​ሻ​ውና በእ​ር​ስዋ ላይ ያለ​ችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተ​ገዙ ናቸው።”

33 ያዕ​ቆ​ብም ትእ​ዛ​ዙን ለል​ጆቹ ተና​ግሮ በፈ​ጸመ ጊዜ እግ​ሮ​ቹን በአ​ል​ጋው ላይ ዘር​ግቶ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos