Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 118 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


አሌፍ።

1 በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ንጹ​ሓን የሆኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።

2 ምስ​ክ​ሩን የሚ​ፈ​ልጉ፥ በፍ​ጹም ልብ የሚ​ሹት ብፁ​ዓን ናቸው፤

3 ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን በመ​ን​ገዱ አይ​ሄ​ዱም።

4 ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እጅግ ይጠ​ብቁ ዘንድ አንተ አዘ​ዝህ።

5 ሥር​ዐ​ት​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ የሚ​ቀ​ናስ ከሆነ መን​ገዴ ይቅና።

6 ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም።

7 አቤቱ፥ የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

8 ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ጣ​ለኝ።


ቤት።

9 ጐል​ማሳ መን​ገ​ዱን በምን ያቀ​ናል? ቃል​ህን በመ​ጠ​በቅ ነው።

10 በፍ​ጹም ልቤ ፈለ​ግ​ሁህ፥ ከት​እ​ዛ​ዝህ አታ​ር​ቀኝ።

11 አን​ተን እን​ዳ​ል​በ​ድል፥ ቃል​ህን በልቤ ሰወ​ርሁ።

12 አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

13 የአ​ፍ​ህን ፍርድ ሁሉ በከ​ን​ፈሬ ነገ​ርሁ።

14 እንደ ብል​ጥ​ግና ሁሉ በም​ስ​ክ​ርህ መን​ገድ ደስ አለኝ።

15 ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ሰ​ልሁ፥ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ።

16 ትእ​ዛ​ዞ​ች​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ህ​ንም አል​ረ​ሳም።


ጋሜል።

17 ሕያው እን​ድ​ሆን ቃል​ህ​ንም እን​ድ​ጠ​ብቅ ለባ​ሪ​ያህ ስጠው።

18 ዓይ​ኖ​ችን ክፈት፥ ከሕ​ግ​ህም ድንቅ ነገ​ርን አያ​ለሁ።

19 እኔ በም​ድር ስደ​ተኛ ነኝ፤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን ከእኔ አት​ሰ​ውር።

20 ነፍሴ ሁል​ጊዜ ፍር​ድ​ህን እጅግ ናፈ​ቀች። ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ገሠ​ጽ​ኻ​ቸው፥

21 ከት​እ​ዛ​ዛ​ትህ የሚ​ርቁ ርጉ​ማን ናቸው።

22 ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ።

23 አለ​ቆች ደግሞ ተቀ​ም​ጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪ​ያህ ግን ፍር​ድ​ህን ያሰ​ላ​ስል ነበር።

24 ምስ​ክ​ር​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው፥ ሥር​ዐ​ት​ህም መካሬ ነው።


ዳሌጥ።

25 ሰው​ነቴ ወደ ምድር ተጣ​በ​ቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።

26 መን​ገ​ድ​ህ​ንና ምስ​ክ​ር​ህን ነገ​ርሁ፥ ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ።

27 የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።

28 ከኀ​ዘን የተ​ነሣ ሰው​ነቴ አን​ቀ​ላ​ፋች፤ በቃ​ልህ አጠ​ን​ክ​ረኝ።

29 የዐ​መ​ፃን መን​ገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕ​ግ​ህም ይቅር በለኝ፤

30 የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ መረ​ጥሁ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አል​ረ​ሳ​ሁም።

31 አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ህን ተከ​ተ​ልሁ፥ አታ​ሳ​ፍ​ረኝ።

32 ልቤን ባሰ​ፋ​ኸው ጊዜ፥ በት​እ​ዛ​ዝህ መን​ገድ ሮጥሁ።


ሄ።

33 አቤቱ፥ የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ አስ​ተ​ም​ረኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም እፈ​ል​ጋ​ታ​ለሁ።

34 እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ሕግ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በፍ​ጹም ልቤም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ።

35 እር​ስ​ዋን ወድ​ጃ​ለ​ሁና የት​እ​ዛ​ዝ​ህን መን​ገድ ምራኝ።

36 ልቤን ወደ ምስ​ክ​ርህ መልስ፥ ወደ ቅሚ​ያም አይ​ሁን።

37 ከንቱ ነገ​ርን እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቼን መልስ፤ በመ​ን​ገ​ድ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።

38 እን​ዲ​ፈ​ራህ ለባ​ሪ​ያህ በቃ​ልህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን አጽና።

39 ፍር​ድህ መል​ካም ነውና የተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁ​ትን ስድብ ከእኔ አርቅ።

40 እነሆ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ናፈ​ቅሁ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።


ዋው።

41 አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ይም​ጣ​ልኝ፥ አቤቱ፥ ማዳ​ንህ እንደ ቃልህ ነው።

42 በቃ​ልህ ታም​ኛ​ለ​ሁና ለሚ​ሰ​ድ​ቡኝ በነ​ገር እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

43 በፍ​ር​ድ​ህም ታም​ኛ​ለ​ሁና የእ​ው​ነ​ትን ቃል ከአፌ ፈጽ​መህ አታ​ርቅ።

44 ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ሁል​ጊዜ ሕግ​ህን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።

45 ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና አስ​ፍቼ እሄ​ዳ​ለሁ።

46 በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ምስ​ክ​ር​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ፥ አላ​ፍ​ር​ምም፤

47 እጅ​ግም የወ​ደ​ድ​ኋ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ።

48 እጆ​ቼ​ንም ወደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው ወደ ትእ​ዛ​ዛ​ትህ አነ​ሣ​ለሁ፤ ፍር​ድ​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።


ዛይ።

49 ለባ​ሪ​ያህ ተስፋ ያስ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ቃል​ህን አስብ።

50 ቃልህ ሕያው አድ​ር​ጎ​ኛ​ልና። ይህች በመ​ከ​ራዬ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ።

51 ትዕ​ቢ​ተ​ኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕ​ግህ አል​ራ​ቅ​ሁም።

52 ከጥ​ንት የነ​በ​ረ​ውን ፍር​ድ​ህን ዐሰ​ብሁ፥ አቤቱ፥ደስ አለኝ።

53 ሕግ​ህን ከተዉ ኃጥ​ኣን የተ​ነሣ ኀዘን ያዘኝ።

54 በእ​ን​ግ​ድ​ነቴ ሀገር ፍር​ድህ መዝ​ሙር ሆነኝ።

55 አቤቱ፥ በሌ​ሊት ስም​ህን ዐሰ​ብሁ፥ ሕግ​ህ​ንም ጠበ​ቅሁ።

56 ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ይህች ሆነ​ች​ልኝ።


ሔት።

57 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግ​ህን ይጠ​ብቁ አልሁ።

58 አቤቱ በፍ​ጹም ልቤ ወደ ፊትህ ለመ​ንሁ፤ እንደ ቃልህ ይቅር በለኝ።

59 ስለ መን​ገ​ዶ​ችህ ዐሰ​ብሁ፥ እግ​ሬ​ንም ወደ ምስ​ክ​ርህ መለ​ስሁ።

60 ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለመ​ጠ​በቅ ጨከ​ንሁ፥ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁ​ምም።

61 የኃ​ጥ​ኣን ገመ​ዶች ተተ​በ​ተ​ቡ​ብኝ፤ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።

62 ስለ ጽድ​ቅህ ፍርድ፥ አመ​ሰ​ግ​ንህ ዘንድ በእ​ኩለ ሌሊት እነ​ሣ​ለሁ።

63 እኔ ለሚ​ፈ​ሩህ ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ባል​ን​ጀራ ነኝ።

64 አቤቱ፥ ይቅ​ር​ታህ በም​ድር ሁሉ ሞላች፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።


ጤት።

65 አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባ​ሪ​ያህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።

66 በት​እ​ዛ​ዛ​ትህ ታም​ኛ​ለ​ሁና መል​ካም ምክ​ር​ንና ጥበ​ብን አስ​ተ​ም​ረኝ።

67 እኔ ሳል​ጨ​ነቅ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ቃል​ህን ጠበ​ቅሁ።

68 አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸ​ር​ነ​ት​ህም ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ።

69 የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ዐመፃ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍ​ጹም ልቤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እፈ​ል​ጋ​ለሁ።

70 ልባ​ቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን ሕግ​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ

71 ፍር​ድ​ህን አውቅ ዘንድ ያስ​ጨ​ነ​ቅ​ኸኝ መል​ካም ሆነ​ልኝ።

72 ከአ​እ​ላ​ፋት ወር​ቅና ብር ይልቅ። የአ​ፍህ ሕግ ይሻ​ለ​ኛል።


ዮድ።

73 እጆ​ችህ ሠሩኝ፥ አበ​ጃ​ጁ​ኝም፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም እማ​ራ​ለሁ።

74 በቃ​ልህ ታም​ኛ​ለ​ሁና የሚ​ፈ​ሩህ እኔን አይ​ተው ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

75 አቤቱ፥ ፍር​ድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በሚ​ገ​ባም እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቅ​ኸኝ ዐወ​ቅሁ።

76 ምሕ​ረ​ትህ ለደ​ስ​ታዬ ይሁ​ነኝ፥ እንደ ቃል​ህም ለባ​ሪ​ያህ ይሁ​ነው።

77 ሕግህ ትም​ህ​ርቴ ነውና ቸር​ነ​ትህ ይም​ጣ​ልኝ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ልኑር።

78 ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ዐመ​ፃን መክ​ረ​ው​ብ​ኛ​ልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።

79 የሚ​ፈ​ሩ​ህና ምስ​ክ​ሮ​ች​ህን የሚ​ያ​ውቁ ወደ እኔ ይመ​ለሱ።

80 እን​ዳ​ላ​ፍር ልቤ በፍ​ር​ድህ ንጹሕ ይሁን።


ካፍ።

81 ነፍሴ ወደ ማዳ​ንህ አለ​ፈች፤ በቃ​ል​ህም ታመ​ንሁ።

82 መቼ ታጽ​ና​ና​ኛ​ለህ እያ​ልሁ ዐይ​ኖቼ ትድ​ግ​ና​ህን በመ​ጠ​በቅ ፈዘዙ።

83 በው​ርጭ እን​ዳለ ረዋት ሆኛ​ለ​ሁና፤ ፍር​ድ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።

84 የባ​ሪ​ያህ ዘመ​ኖች ምን ያህል ናቸው? በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝስ ላይ መቼ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ?

85 ኃጥ​ኣን ዋዛ-ፈዛ​ዛን ነገ​ሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይ​ደ​ለም።

86 ትእ​ዛ​ዝ​ትህ ሁሉ እው​ነት ናቸው፤ በዐ​መፃ አሳ​ድ​ደ​ው​ኛል፤ ርዳኝ።

87 ከም​ድር ሊያ​ጠ​ፉኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን አል​ተ​ው​ሁም።

88 እንደ ምሕ​ረ​ትህ ሕያው አድ​ር​ገኝ፤ የአ​ፍ​ህ​ንም ምስ​ክር እጠ​ብ​ቃ​ለሁ። ላሜድ።

89 አቤቱ፥ ቃልህ በሰ​ማይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።

90 እው​ነ​ትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድ​ርን መሠ​ረ​ት​ሃት፥ እር​ስ​ዋም ትኖ​ራ​ለች።

91 ሁሉን ገዝ​ተ​ሃ​ልና ቀኑ በት​እ​ዛ​ዝህ ይኖ​ራል።

92 ሕግህ ትም​ህ​ርቴ ባይ​ሆን፥ ቀድሞ በጕ​ስ​ቍ​ል​ናዬ በጠ​ፋሁ ነበር።

93 በእ​ርሱ ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ኛ​ልና ፍር​ድ​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ረ​ሳም።

94 እኔ የአ​ንተ ነኝ፥ ፍር​ድ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና አድ​ነኝ።

95 ኃጥ​ኣን ያጠ​ፉኝ ዘንድ ጠበ​ቁኝ፤ ምስ​ክ​ር​ህን አስ​ተ​ው​ያ​ለ​ሁና።

96 የሥ​ራ​ውን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእ​ዛ​ዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።


ሜም።

97 አቤቱ፥ ሕግ​ህን እን​ደ​ምን እጅግ ወደ​ድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትም​ህ​ርቴ ነው።

98 ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለእኔ ነውና ትእ​ዛ​ዝህ ከጠ​ላ​ቶቼ ይልቅ አስ​ተ​ዋይ አደ​ረ​ገኝ።

99 ትእ​ዛ​ዝህ ትም​ህ​ርቴ ነውና ካስ​ተ​ማ​ሩኝ ሁሉ ይልቅ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።

100 ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ይልቅ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።

101 ቃል​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ ከክፉ መን​ገድ ሁሉ እግ​ሬን ከለ​ከ​ልሁ።

102 አንተ አስ​ተ​ም​ረ​ኸ​ኛ​ልና ከፍ​ር​ድህ አል​ራ​ቅ​ሁም።

103 ቃልህ ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማ​ርና ከወ​ለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈ​ጠኝ።

104 ከት​እ​ዛ​ዝህ የተ​ነሣ አስ​ተ​ዋ​ልሁ፤ ስለ​ዚህ የዐ​መ​ፃን መን​ገድ ጠላሁ።


ኖን።

105 ሕግህ ለእ​ግሬ መብ​ራት፥ ለመ​ን​ገ​ዴም ብር​ሃን ነው።

106 የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ እጠ​ብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸ​ና​ሁም።

107 እጅግ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፥ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።

108 አቤቱ፥ ከአፌ የሚ​ወ​ጣ​ውን ቃል ውደድ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

109 ነፍሴ ሁል​ጊዜ በእ​ጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።

110 ኃጥ​ኣን ወጥ​መ​ድን ዘረ​ጉ​ብኝ፤ ከት​እ​ዛ​ዝህ ግን አል​ሳ​ት​ሁም።

111 የልቤ ደስታ ነውና ምስ​ክ​ር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወረ​ስሁ።

112 ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያለ ነቀፋ ትእ​ዛ​ዝ​ህን አደ​ርግ ዘንድ ልቤን መለ​ስሁ።


ሳም​ኬት።

113 ዐመ​ፀ​ኞ​ችን ጠላሁ፥ ሕግ​ህን ግን ወደ​ድሁ።

114 አንተ ረዳ​ቴና መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፥ በቃ​ል​ህም ተማ​መ​ንሁ።

115 እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም ትእ​ዛዝ ልፈ​ልግ።

116 እንደ ቃልህ ተቀ​በ​ለኝ፥ ሕያ​ውም እሆ​ና​ለሁ፤ ከተ​ስ​ፋ​ዬም አታ​ሳ​ፍ​ረኝ።

117 ርዳ​ኝም፥ አድ​ነ​ኝም፥ ሁል​ጊ​ዜም ፍር​ድ​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ።

118 ምኞ​ታ​ቸው ዐመፃ ነውና ከሥ​ር​ዐ​ትህ የሚ​ር​ቁ​ትን ሁሉ አጐ​ሳ​ቈ​ል​ሃ​ቸው።

119 የም​ድር ኃጥ​ኣን ሁሉ ወን​ጀ​ለ​ኞች ናቸው፤ ስለ​ዚህ ምስ​ክ​ር​ህን ወደ​ድሁ።

120 መፈ​ራ​ት​ህን በሥ​ጋዬ ውስጥ አስ​ማማ፤ ከፍ​ር​ድህ የተ​ነሣ ፈር​ቻ​ለ​ሁና።


ዔ።

121 ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ሠራህ፤ ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠኝ።

122 ባሪ​ያ​ህን በመ​ል​ካም ጠብ​ቀው፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም አይ​ጋ​ፉኝ።

123 ዐይ​ኖቼ ለማ​ዳ​ንህ፥ ለጽ​ድ​ቅ​ህም ቃል ፈዘዙ።

124 ለባ​ሪ​ያህ እንደ ምሕ​ረ​ትህ አድ​ርግ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

125 እኔ ባሪ​ያህ ነኝ፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አው​ቃ​ለሁ።

126 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሥራ ጊዜ አለው፥ ሕግ​ህ​ንም ሻሩት።

127 ስለ​ዚህ ከወ​ር​ቅና ከዕ​ንቍ ይልቅ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ወደ​ድሁ።

128 ስለ​ዚህ ወደ ትእ​ዛ​ዝህ ሁሉ አቀ​ናሁ፥ የዐ​መ​ፃ​ንም መን​ገድ ሁሉ ጠላሁ።


ፌ።

129 ምስ​ክ​ርህ ድንቅ ነው፤ ስለ​ዚህ ነፍሴ ፈለ​ገ​ችው።

130 የቃ​ልህ ነገር ያበ​ራል፥ ሕፃ​ና​ት​ንም አስ​ተ​ዋ​ዮች ያደ​ር​ጋል።

131 አፌን ከፈ​ትሁ፥ ልቡ​ና​ዬ​ንም አሰ​ፋሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ወድ​ጃ​ለ​ሁና።

132 ስም​ህን ለሚ​ወ​ድዱ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፥ ይቅ​ርም በለኝ።

133 መን​ገ​ዴ​ንና አካ​ሄ​ዴን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኀጢ​አ​ትም ሁሉ ድል አይ​ን​ሳኝ።

134 ከሰው ቅሚያ አድ​ነኝ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ ።

135 በባ​ሪ​ያህ ላይ ፊት​ህን አብራ፥ ፍር​ድ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

136 ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ሁ​ምና የውኃ ፈሳሽ ከዐ​ይ​ኖች ፈሰሰ።


ጻዴ።

137 አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍር​ድ​ህም ቅን ነው።

138 ምስ​ክ​ር​ህን በጽ​ድቅ አዘ​ዝህ፥ እጅ​ግም ቅን ነው።

139 ጠላ​ቶቼ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ረስ​ተ​ዋ​ልና የቤ​ትህ ቅን​ዓት አቀ​ለ​ጠኝ።

140 ቃልህ እጅግ የጋለ ነው፥ ባሪ​ያህ ግን ወደ​ደው።

141 እኔ ታና​ሽና የተ​ና​ቅሁ ነኝ፥ ሕግ​ህን ግን አል​ረ​ሳ​ሁም።

142 ጽድ​ቅ​ህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ጽድቅ ነው፥ ቃል​ህም የታ​መነ ነው።

143 መከ​ራና ችግር አገ​ኙኝ፤ ትእ​ዛ​ዝህ ግን ትም​ህ​ርቴ ነው።

144 ምስ​ክ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እው​ነት ነው፤ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም አኑ​ረኝ።


ቆፍ።

145 በፍ​ጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ ስማኝ፤ ፍር​ድ​ህ​ንም ፈለ​ግሁ።

146 ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ስማኝ አድ​ነ​ኝም። ምስ​ክ​ር​ህ​ንም ልጠ​ብቅ።

147 ወደ ተራ​ሮች ደረ​ስሁ፥ ጮኽ​ሁም። ቃል​ህን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።

148 ዐይ​ኖቼ ለመ​ማ​ለድ ደረሱ፥ ቃል​ህን እና​ገር ዘንድ።

149 አቤቱ፥ እንደ ይቅ​ር​ታህ ቃሌን ስማ፤ እንደ ፍር​ድህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።

150 በዐ​መፃ የከ​በ​ቡኝ ቀረቡ፥ ከሕ​ግህ ግን ራቁ።

151 አቤቱ አንተ ቅርብ ነህ፥ መን​ገ​ዶ​ች​ህም ሁሉ የቀኑ ናቸው።

152 ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ መሠ​ረ​ት​ሃ​ቸው ከቀ​ድሞ ጀምሮ ምስ​ክ​ሮ​ች​ህን ዐወ​ቅሁ።


ሬስ።

153 ሕግ​ህን አል​ረ​ሳ​ሁ​ምና ችግ​ሬን ተመ​ል​ከት፥ አድ​ነ​ኝም።

154 ፍር​ዴን ፍረድ አድ​ነ​ኝም፤ ስለ ቃል​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።

155 ሕይ​ወት ከኃ​ጥ​ኣን የራቀ ነው፥ ፍር​ድ​ህን አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና።

156 አቤቱ፥ ይቅ​ር​ታህ እጅግ የበዛ ነው፤ እንደ ፍር​ድ​ህም ሕያው አድ​ር​ገኝ።

157 የከ​በ​ቡ​ኝና ያስ​ጨ​ነ​ቁኝ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከም​ስ​ክ​ርህ ግን ፈቀቅ አላ​ል​ሁም።

158 ቃል​ህን አል​ጠ​በ​ቁ​ምና ሰነ​ፎ​ችን አይቼ አዘ​ንሁ።

159 ትእ​ዛ​ዝ​ህን እንደ ወደ​ድሁ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ፥ በይ​ቅ​ር​ታህ ሕያው አድ​ር​ገኝ።

160 የቃ​ልህ መጀ​መ​ሪያ እው​ነት ነው፥ ፍር​ድ​ህም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እው​ነት ነው።


ሣን።

161 አለ​ቆች በከ​ንቱ አሳ​ደ​ዱኝ፤ ከቃ​ልህ የተ​ነሣ ግን ልቤ ደን​ገ​ጠ​ብኝ።

162 ብዙ ምርኮ እን​ዳ​ገኘ በቃ​ልህ ደስ አለኝ።

163 ዐመ​ፃን ጠላሁ ተጸ​የ​ፍ​ሁም፤ ሕግ​ህን ግን ወደ​ድሁ።

164 ስለ እው​ነት ፍር​ድህ ሰባት ጊዜ በቀን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

165 ስም​ህን ለሚ​ወ​ድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕን​ቅ​ፋት የለ​ባ​ቸ​ውም።

166 አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ተስፋ አደ​ረ​ግሁ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህ​ንም ጠበ​ቅሁ።

167 ነፍሴ ምስ​ክ​ር​ህን ጠበ​ቀች፥ እጅ​ግም ወደ​ደ​ችው።

168 አቤቱ፥ መን​ገ​ዶ​ችህ ሁሉ በፊ​ትህ ናቸ​ውና። ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ምስ​ክ​ር​ህን ጠበ​ቅሁ።


ታው።

169 አቤቱ፥ ልመ​ናዬ ወደ አንተ ትቅ​ረብ፤ እንደ ቃል​ህም አስ​ተ​ዋይ አድ​ር​ገኝ።

170 አቤቱ፥ ምል​ጃዬ ወደ ፊትህ ትድ​ረስ፤ እንደ ቃል​ህም አድ​ነኝ።

171 ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረ​ኸ​ኛ​ልና ከን​ፈ​ሮች ምስ​ጋ​ና​ህን ይና​ገ​ራሉ።

172 ትእ​ዛ​ዛ​ትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸ​ውና፥ አን​ደ​በቴ ቃል​ህን ተና​ገረ።

173 ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን ወድ​ጃ​ለ​ሁና ቀኝህ የሚ​ያ​ድ​ነኝ ይሁን።

174 አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ናፈ​ቅሁ፤ ሕግ​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው።

175 ነፍሴ ትኑ​ር​ልኝ ላመ​ስ​ግ​ን​ህም፥ ፍር​ድ​ህም ይር​ዳኝ።

176 እንደ ጠፋ በግ ተዘ​ነ​ጋሁ፤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን አል​ረ​ሳ​ሁ​ምና ባሪ​ያ​ህን ፈል​ገው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos