Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሮሜ 14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ባል​ን​ጀ​ራን ስለ ማጽ​ና​ናት

1 እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።

2 ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ።

3 የሚ​በ​ላ​ውም የማ​ይ​በ​ላ​ውን አይ​ና​ቀው፤ የማ​ይ​በ​ላ​ውም የሚ​በ​ላ​ውን አይ​ን​ቀ​ፈው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አው​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።

4 እን​ግ​ዲህ የሌ​ላ​ውን ሎሌ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወ​ድቅ ለጌ​ታው ነው። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ነ​ሣው ይች​ላ​ልና ይቆ​ማል።

5 ከቀን ቀን የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ዘወ​ት​ርም የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ነገር ግን ሁሉም ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ።

6 አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል።

7 ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም ለራሱ የሚ​ኖር፥ ለራ​ሱም የሚ​ሞት የለም።

8 በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ኖ​ራ​ለን፤ ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ግ​ዲህ በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነን።

9 ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።

10 እን​ግ​ዲህ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ፈ​ርድ አንተ ምን​ድን ነህ? ወን​ድ​ም​ህ​ንስ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ምን​ድን ነህ? ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይሰ​ግ​ዳል፤ አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይገ​ዛል።”

12 እነሆ፥ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ም​ን​መ​ረ​መር ታወቀ።


ለባ​ል​ን​ጀራ ዕን​ቅ​ፋት ስላ​ለ​መ​ሆን

13 እን​ግ​ዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ነ​ቃ​ቀፍ፤ ይል​ቁ​ንም ለወ​ን​ድም እን​ቅ​ፋ​ትን ወይም ማሰ​ና​ከ​ያን ማንም እን​ዳ​ያ​ኖር ይህን ዐስቡ።

14 በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እን​ደ​ሌለ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ሆኜ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ተረ​ድ​ቼ​አ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ማና​ቸ​ውም ነገር ርኩስ እን​ደ​ሚ​ሆን ለሚ​ያ​ስብ ያ ለእ​ርሱ ርኩስ ነው።

15 በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን?

16 እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን የሰ​ጠ​ንን መል​ካ​ሙን ነገር አታ​ሰ​ድቡ።

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።

18 እን​ዲህ አድ​ርጎ ለክ​ር​ስ​ቶስ የሚ​ገዛ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝና በሰ​ውም ዘንድ የተ​መ​ረጠ ነው።

19 አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።

20 በመ​ብል ምክ​ን​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍጥ​ረት አና​ፍ​ርስ፤ ለን​ጹ​ሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰ​ውስ ክፉው ነገር በመ​ጠ​ራ​ጠር መብ​ላት ነው።

21 ለወ​ን​ድም ዕን​ቅ​ፋት ከመ​ሆን ሥጋን አለ​መ​ብ​ላት ወይ​ን​ንም አለ​መ​ጠ​ጣት ይሻ​ላል።

22 እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።

23 የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ቢበላ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታል፤ በማ​መን አል​ሆ​ነ​ምና፤ ያለ እም​ነ​ትም የሚ​ደ​ረግ ሁሉ ኀጢ​አ​ትና በደል ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos