1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።
2 ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በልብሱ መደረቢያ ላይ፥ እስከሚወርደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እንደሚፈስ ሽቱ ነው።
3 በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔምም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም አዝዞአልና።