Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘዳግም 34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሙሴ መሞ​ትና መቀ​በር

1 ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤

2 የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ምድር ሁሉ፥ የም​ና​ሴ​ንም ምድር ሁሉ፥ እስከ ምዕ​ራ​ብም ባሕር ድረስ ያለ​ውን የይ​ሁ​ዳን ምድር ሁሉ፤

3 ምድረ በዳ​ውን፥ የኢ​ያ​ሪ​ኮን ዙሪያ፥ እስከ ሴይር ዙሪያ ያለ​ው​ንም የፊ​ን​ቆ​ንን ከተማ አሳ​የው፤

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው።

5 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በዚያ በሞ​ዓብ ምድር ሞተ።

6 በቤተ ፌጎ​ርም አቅ​ራ​ቢያ በና​ባው ምድር ቀበ​ሩት፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃ​ብ​ሩን ማንም የሚ​ያ​ውቅ የለም።

7 ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።

9 ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት እንደ ተና​ገ​ረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አል​ተ​ነ​ሣም፤

11 በግ​ብፅ ምድር በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከው ያለ፥

12 በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በታ​ላቅ ተአ​ምር ሁሉና በጸ​ናች እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አል​ተ​ነ​ሣም።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos