እስራኤልም ዮሴፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ዘኍል 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እኛ እናጠፋቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጊዜአቸው አልፎባቸዋል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው” ብለው ተናገሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። |
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳን የሚዋጋልንም አምላካችን እግዚአብሔር ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።
አይችም ተነሣሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን አምላካችንን አስቡ፤ ስለ ወንድሞቻችሁም፥ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ስለ ሚስቶቻችሁም፥ ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ” አልኋቸው።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
በምድርም ከአለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ ተለይተን እንከብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ በእውነት ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል?” አለው።
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቍጥር ጥቂት የነበርህ እስራኤል ሆይ፥ እኔ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ ፊት አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ፥ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ከሰልፍ የሸሹ ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል፤ የሞአብንም ማዕዘን፥ የሚጮኹ ልጆችንም ራስ በልቶአል።
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤ አለቆቻቸውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች።
እግዚአብሔር ከግብፅ መርቶ አውጥቶታል፤ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር አለው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፤ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፤ በፍላጾቹም ጠላቱን ይወጋዋል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
እነሆ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ምድሪቱን በፊታችሁ እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፤ ውረሷት፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
ጽና፤ በርታ፤ አትፍራ፤ ከፊታቸውም አትደንግጥ፤ አትድከም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ አይጥልህም፤ አይተውህምም።
በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አይጥልህም፤ አይተውህም፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ’ ” አለው።
ከፊታቸው አትደንግጥ፤ አምላክህ እግዚአብሔር፥ ከአንተ ጋር ነውና፥ እርሱም አምላክህ እግዚአብሔር ታላቅና ጽኑዕ ነውና።
“አምላክህን እግዚአብሔርን በምድረ በዳ ምን ያህል እንዳሳዘንኸው፥ ከግብፅ ሀገር ከወጣህበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስብ፤ አትርሳም።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የሚቋቋምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ ቸልም አልልህም።
አሁን እንግዲህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን፥ ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ አጠፋቸዋለሁ።”