ዘፀአት 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 በምድርም ከአለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ ተለይተን እንከብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ በእውነት ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል?” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 አንተ ከእኛ ጋራ ካልሄድህ፣ አንተ በእኔና በሕዝብህ መደሰትህን ሌላው እንዴት ያውቃል? እኔንና ሕዝብህንስ በገጸ ምድር ከሚገኙት ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ ልዩ የሚያደርገን ሌላ ምን አለ?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? እኔና ሕዝብህ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር በመውጣትህ አይደለምን?” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆነ በሕዝብህም ሆነ በእኔና በሕዝብህ ደስ መሰኘትህን ሰዎች ሁሉ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? እኛን በምድር ላይ ካሉት ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየ የሚያደርገን የአንተ ከእኔና ከሕዝብህ ጋር መሆን አይደለምን?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው። Ver Capítulo |
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በባሪያህ በሙሴ እጅ እንደ ተናገርህ ርስት ይሆኑህ ዘንድ ከምድር አሕዛብ ሁሉ ለይተሃቸዋልና።” ያንጊዜም ሰሎሞን ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ስለዚያ ቤት እንዲህ ሲል ተናገረ። “እግዚአብሔር በሰማይ ፀሐይን አሳየ፤ እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናገረ፤ ቤቴን ሥራ፤ በመታደስም ለመኖር ለራስህ ጥሩ ቤትን ሥራ፤” ይህችስ በመሐልይ መጽሐፍ የተጻፈች አይደለምን?