መዝሙር 121 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የዳዊት የመዓርግ መዝሙር። 1 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ። 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ። 3 ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት። 4 እንደ እርሷ ያሉት በአንድነት ከእርሷ ጋር ናቸው። አቤቱ፥ ለስምህ ይገዙ ዘንድ፥ ለእስራኤል ምስክር የሚሆኑ የእግዚአብሔር ወገኖች አሕዛብ ወደዚያ ይወጣሉና። 5 ለመፍረድ ዙፋኖቻቸውን በዚያ አስቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች። 6 የኢየሩሳሌም ደኅንነትዋን፥ ተነጋገሩ። ስምህን ለሚወድዱ ደስታቸው ነው። 7 በኀይልህ ሰላም ይሁን፥ በክብርህ ቦታ ደስታ አለ። 8 ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ ስለ አንቺም፥ ሰላምን ይናገራሉ። 9 ስለ አምላኬ ስለ እግዚአብሔር ቤት ደኅንነትሽን ፈለግሁ። |