Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 14:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አታ​ምፁ፤ እኛ እና​ጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ንና የም​ድ​ሪ​ቱን ሰዎች አት​ፍሩ፤ ጊዜ​አ​ቸው አል​ፎ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኛ ጋር ነው፤ አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 14:9
50 Referencias Cruzadas  

አትፍራቸው፤ አምላክህ እግዚአብሔር በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ያደረገውን አስታውስ።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?


ቈራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ፤ ከእነርሱም የተነሣ ከቶ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ አይጥላችሁም፤ አይተዋችሁም።”


ሌዋታን የተባለውን የባሕር ዘንዶ ራስ ቀጠቀጥህ፤ ሥጋውንም በበረሓ ለሚኖሩ ፍጥረቶች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው።


ከእርሱ ጋር ያለው ኀይል ሰብአዊ ኀይል ነው፤ ከእኛ ጋር ሆኖ የሚረዳንና የሚዋጋልን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤” ሕዝቡም ንጉሡ በተናገረው በዚህ ቃል ተበረታታ።


በዚህ ጦርነት ላይ የምትዋጉ እናንተ አይደላችሁም፤ ስፍራ ስፍራችሁን ይዛችሁ ብቻ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር ድልን እንደሚያጐናጽፋችሁ ታያላችሁ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! ሳታመነቱና በፍርሃት ሳትሸበሩ ነገ በቀጥታ ሄዳችሁ ተዋጉ! እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል!’ ”


ራሱ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይመራሃል፤ አይጥልህም ከቶም አይተውህም፤ ስለዚህ አትፍራ፤ ተስፋም አትቊረጥ።”


ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል።


አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤


እግዚአብሔር ጠባቂህ ነው፤ በቀኝህም ሆኖ ያጠላልሃል።


“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።


“እግዚአብሔር አምላክህን በበረሓ እንዴት እንዳስቈጣኸው ከቶ አትርሳ፤ የግብጽን ምድር ለቀህ ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ እስከ መጣህበት እስከ አሁን ድረስ በእርሱ ላይ ዐምፀሃል።


“ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በማመፅ ወደዚያች ምድር መግባትን አልወደዳችሁም።


ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ምንም እኛ በአንተ ላይ ብናምፅ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ።


ከተገደሉትና ከተማረኩት ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤ ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’


ስለዚህም እነዚህን ሕዝቦች አትፍራ፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ነው፤ እርሱ ታላቅና መፈራትም የሚገባው አምላክ ነው።


ተመልከቱ፤ አገሪቱ ይህችውላችሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ገብታችሁ ውረሱአት፤ በመፍራትም ተስፋ አትቊረጡ።’


እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


በሽሽት የደከሙ ስደተኞች በሐሴቦን ጥላ ሥር ተጠልለዋል፤ ይህም የሆነው እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሲሆን ቤቶች ወጥቶ የሞአብን ግንባር ቀደም ሠራዊትና ደጋፊ መሪዎችዋን አቃጥሎአል።


ሆኖም እነርሱ የእርሱን ቅዱስ መንፈስ አሳዘኑ፤ ስለዚህ እሱ በእነርሱ ላይ ተነሥቶ ቀጣቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ ትል ደካማ የሆንክ እስራኤል ሆይ! እኔ ስለምረዳህ አትፍራ፤ የምታደግህ የእስራኤል ቅዱስ እኔ ነኝ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ስሙ፤ ምድርም አድምጪ፤ ተንከባክቤ ያሳደግኋቸው ልጆች ዐመፀኞች ሆኑብኝ፤


መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥


የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤


የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”


የዮሴፍ ዘሮች ደግሞ በቤቴል ላይ ዘመቱ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፤


ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆነ በሕዝብህም ሆነ በእኔና በሕዝብህ ደስ መሰኘትህን ሰዎች ሁሉ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? እኛን በምድር ላይ ካሉት ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየ የሚያደርገን የአንተ ከእኔና ከሕዝብህ ጋር መሆን አይደለምን?”


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤


“እኛ ግን ክፉዎችና ዐመፀኞች ሆነን ኃጢአት በመሥራት በድለናል፤ ሕግህንና ትእዛዞችህን ከመፈጸም ቸል ብለናል።


“ነገር ግን እኔ እንዲህ ብዬ ነገርኳችሁ፤ ‘ከእነዚህ ሕዝብ የተነሣ አትፍሩ፤ አትሸበሩም፤


ሕዝቡ ተጨንቀው ስላየሁ፥ እነርሱንና መሪዎቻቸውን፥ ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ሁሉ “ከጠላቶቻችን የተነሣ አትፍሩ፤ ምን ያኽል ታላቅና ግርማው የሚያስፈራ አምላክ እንዳለንና እርሱ ስለ ወገኖቻችሁ፥ ስለ ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ስለ ቤት ንብረታችሁም እንደሚዋጋላችሁ አስታውሱ” አልኳቸው።


አሁን እንደምትፈሩት የባቢሎንን ንጉሥ ከእንግዲህ ወዲያ አትፍሩት፤ እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ ከእርሱ ኀይል እታደጋችኋለሁ፤


ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ! ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የሚያደርገውን ዛሬ ታያላችሁ፤ እነዚህን ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም።


ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”


ስለዚህ ሙሴ ይህንኑ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እያንዳንዱም መሪ በትሩን አምጥቶ ሰጠው፤ ስለያንዳንዱ የነገድ መሪ የሚሰጠው አንዳንድ በትር ሆኖ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት በትሮች ቀረቡ፤ ከእነዚያም በትሮች መካከል የአሮን በትር ነበረች፤


በሰፈሩበት ቦታ ውሃ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰብስበው፥


አሁን እንግዲህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን በሰጠኝ ተስፋ መሠረት ይህን ኮረብታማ አገር ስጠኝ፤ ዐናቃውያን ከታላላቅ የተመሸጉ ከተሞች ጋር እንደ ነበሩ በዚያን ቀን ሰምተሃል፤ እግዚአብሔር እንዳለ እርሱ ከእኔ ጋር ሆኖ አሳድዳቸዋለሁ።


ኑ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ፤ በምድር ላይ ያመጣውን ጥፋት ተመልከቱ።


በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስላልተማመኑ መልካሚቷን ምድር ናቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios