Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ ካህ​ናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ይጮ​ኻሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አይ​በ​ጃ​ች​ሁ​ምና ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አቷጉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ መሪያችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ አትዋጉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነሆም፥ ጌታ በእኛ ላይ አለቃ ነው፥ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፥ በእናንተም ላይ የጦርነት ማስጠንቀቅያ ድምፅ ያሰማሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ! አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከጌታ ጋር አትዋጉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኸሉ። የእስራኤ ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:12
27 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ልጅ በአ​ዛ​ር​ያስ ላይ መጣ፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ ፊት ቆመና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? መል​ካ​ምም አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተዋ​ችሁ እርሱ ትቶ​አ​ች​ኋል” አላ​ቸው።


ከእ​ርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚ​ረ​ዳን የሚ​ዋ​ጋ​ል​ንም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።” ሕዝ​ቡም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ቃል ተጽ​ናና።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን?


በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤


“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?


በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምክ​ርን ብት​መ​ክ​ሩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ራ​ች​ሁን ይለ​ው​ጣል፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ትም ነገር አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።


ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይደ​ር​ቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበ​ቀ​ለ​ውስ ቅጠሉ ይጠ​ወ​ልግ ዘንድ ሥሩን አይ​ነ​ቅ​ለ​ው​ምን? ፍሬ​ው​ንስ አይ​ለ​ቅ​መ​ው​ምን? ሥሩም የተ​ነ​ቀ​ለው በብ​ርቱ ክን​ድና በብዙ ሕዝብ አይ​ደ​ለም።


በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።


ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።


ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመጣ ከሆነ ግን ልታ​ፈ​ር​ሱት አት​ች​ሉም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር እን​ደ​ሚ​ጣላ አት​ሁኑ።”


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


ዕውር በጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​ዳ​ብስ በቀ​ትር ጊዜ ትዳ​ብ​ሳ​ለህ፤ መን​ገ​ድ​ህም የቀና አይ​ሆ​ንም፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ የተ​ገ​ፋህ፥ የተ​ዘ​ረ​ፍ​ህም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም የለም።


ብዙ ልጆ​ችን ወደ ክብር ሲያ​መጣ የመ​ዳ​ና​ቸ​ውን ራስ በመ​ከራ ይፈ​ጽም ዘንድ ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ሁሉ በእጁ ለተ​ያዘ፥ በእ​ር​ሱም ሁሉ ለሆነ ለእ​ርሱ ተገ​ብ​ቶ​ታ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos