ለኢዮአካዝም ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥርም ሰረገሎች፥ ከዐሥር ሺህም እግረኞች በቀር ሕዝብ አልቀረለትም፤ የሶርያ ንጉሥ አጥፍቶአቸዋልና፥ በአውድማም እንዳለ ዕብቅ አድቅቆአቸዋልና።
ሆሴዕ 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ ከግብፅ ጕስቍልና የተነሣ ሸሽተው ይሄዳሉ፤ ሜምፎስም ትቀበላቸዋለች፤ በማከማስም ይቀብሩአቸዋል፤ ጥፋትም ወርቃቸውን ይወርሳል፥ እሾህም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ሄዱ፥ ግብጽም ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፥ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሳል፥ እሾህም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል። |
ለኢዮአካዝም ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥርም ሰረገሎች፥ ከዐሥር ሺህም እግረኞች በቀር ሕዝብ አልቀረለትም፤ የሶርያ ንጉሥ አጥፍቶአቸዋልና፥ በአውድማም እንዳለ ዕብቅ አድቅቆአቸዋልና።
ወደ ሰማይ የወጣ፥ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በብብቱ የሰበሰበ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርንስ ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።
በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።
አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ ዕወቁ።”
በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ፥ በሜምፎስም፥ በፋቱራም ሀገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
ወደ ግብፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለጥፋት፥ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
ኢየሩሳሌምንም በመዐት እንደ ጐበኘሁ፥ እንዲሁ በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እጐበኛለሁ።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
አንቺ በግብፅ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ! ሜምፎስ ባድማ ትሆናለችና፥ የሚቀመጥባትም አይገኝምና ለፍልሰት የሚሆን ዕቃ አዘጋጂ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ፤ ምስሎቹንም ከሜምፎስ እሽራለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በግብፅ ምድር አለቃ አይሆንም፤ በግብፅ ምድር ላይም ፍርሀትን አደርጋለሁ።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።
እንደ ወፍ ከግብፅ፥ እንደ ርግብም ከአሶር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤ ወደ ቤታቸውም እመልሳቸዋለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! እኔንም ስለ በደሉ ደንግጠዋል! እኔ ታደግኋቸው፤ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ።
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ከምላሳቸው ስንፍና የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህም በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
የእስራኤልም ሰዎች ወደ እነርሱ መሄድ እንደሚያስጨንቃቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋሻና በግንብ፥ በገደልና በቋጥኝ፥ በጕድጓድም ውስጥ ተሸሸጉ።