Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 26:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም ባድማ ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ይፈርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 26:33
34 Referencias Cruzadas  

“የማ​ይ​በ​ድ​ልም ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ህም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላ​ቶች ሀገር ቢማ​ረ​ኩም፥


የን​ጉ​ሡም የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


“እና​ንተ ግን ብት​መ​ለሱ፥ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ብት​ተዉ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥


እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


“አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ደነ​ገጡ፥ እንደ ሰካ​ራ​ምም ተን​ገ​ዳ​ገዱ፥ ጥበ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ተዋጠ።


ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።


የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።


ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።


እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”


ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው እብቅ እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።


እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”


እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ላ​ወ​ቋ​ቸው አሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እስከ አጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ በስተ ኋላ​ቸው ሰይ​ፍን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውር​ደ​ቷና ስለ ባር​ነቷ ብዛት ተሰ​ደ​ደች፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተቀ​መ​ጠች፤ ዕረ​ፍ​ትም አላ​ገ​ኘ​ችም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አት መካ​ከል ያዙ​ዋት።


ሳም​ኬት። እና​ንተ ከር​ኩ​ሳን ራቁ፥ አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉ​አ​ቸው፤ አት​ን​ኩ​አ​ቸ​ውም። ታው​ከ​ዋ​ልና ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ኖ​ሩ​ባት ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው።


ዔ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፍ​ላ​ቸው ነበረ። ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም፤ የካ​ህ​ና​ቱን ፊት አላ​ፈ​ሩም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም አላ​ከ​በ​ሩም።


ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


ደግ​ሞም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ እጄን አነ​ሣሁ።


ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል።


የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ተማ​ር​ከው ቢሄዱ በዚያ ሰይ​ፍን አዝ​ዛ​ታ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ዐይ​ኔ​ንም ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት በእ​ነ​ርሱ ላይ እጥ​ላ​ለሁ።”


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos