Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እንደ ወፍ ከግ​ብፅ፥ እንደ ርግ​ብም ከአ​ሶር ምድር እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ይወ​ጣሉ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንደ ወፍ ከግብጽ፣ እንደ ርግብ ከአሦር፣ እየበረሩ ይመጣሉ፤ እኔም በቤታቸው አኖራቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንደ ወፍም ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በቤታቸውም አኖራቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደ ወፍ ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር እየበረሩ ይመጣሉ፤ ወደ መኖሪያቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ይህን የምናገር እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንደ ወፍም ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፥ በቤታቸውም አኖራቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 11:11
17 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


እንደ ደመና፥ ከጫ​ጩ​ቶ​ችዋ ጋር ወደ መስ​ኮቷ እን​ደ​ም​ት​ገባ ርግ​ብም የሚ​በ​ርሩ እነ​ዚህ እነ​ማን ናቸው?


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።


አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከገ​ቡ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከስ​ፍ​ራም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በኖ​ሩ​ባት፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆብ በሰ​ጠ​ኋት ምድር ይኖ​ራሉ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አለቃ ይሆ​ና​ቸ​ዋል።


ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።


ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ።


“ነገር ግን በጽ​ዮን ተራራ ላይ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ሰዎች የወ​ረ​ሱ​አ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ።


ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፣ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣


አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos