Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 11:11
69 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብጽ ከተሞች፥ ከግብጽ እስከ ወንዙ፥ ከባሕርም እስከ ባሕር፥ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ወደ አንቺ ይመጣሉ።


ከዚህ በኋ​ላም መላው እስ​ራ​ኤል ይድ​ናሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፥ “አዳኝ ከጽ​ዮን ይወ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያስ​ወ​ግ​ዳል።


በዚ​ያም ጊዜ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅሬታ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት የዳ​ኑት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በአ​ቈ​ሰ​ሉ​አ​ቸው ላይ አይ​ደ​ገ​ፉም፤ ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በእ​ው​ነት ይደ​ገ​ፋሉ።


እንደ ወፍ ከግ​ብፅ፥ እንደ ርግ​ብም ከአ​ሶር ምድር እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ይወ​ጣሉ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።


በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በባ​ሕር ደሴ​ቶች ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይከ​ብ​ራል።


እንደ ሔማት አር​ፋድ፥ እንደ አር​ፋድ ሴፋ​ሩ​ሔም፥ እንደ ሴፋ​ሩ​ሔም ካሌና፥ እንደ ካሌ​ናም ደማ​ስቆ፥ እንደ ደማ​ስ​ቆም ሰማ​ርያ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከም​ሥ​ራ​ቅም ተነ​ሥ​ተው በሄዱ ጊዜ በሰ​ና​ዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።


የግ​ዛ​ቱም መጀ​መ​ሪያ በሰ​ና​ዖር ሀገር ባቢ​ሎን፥ ኦሬክ፥ አር​ካድ፥ ካሌ​ድን ናቸው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ ጊዜ ግን ያ መጋ​ረጃ ከእ​ነ​ርሱ ይር​ቃል።


የእ​ነ​ርሱ መው​ጣት ለዓ​ለም ዕርቅ ከሆነ ይል​ቁ​ንም መመ​ለ​ሳ​ቸው ምን ይሆን? ከሙ​ታን በመ​ነ​ሣት የሚ​ገኝ ሕይ​ወት ነው።


ደግሞም በዳርቻዋ ባለችው በሐማት ላይ፥ እጅግ ጠቢበኞች በሆኑ በጢሮስና በሲዶና ላይ ነው።


እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፣ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።


ጳት​ሮ​ስ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጣ​ኔ​ዎ​ስም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዲ​ዮ​ስ​ጶ​ሊን ላይም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ከባ​ሳን ኮም​ቦል መቅ​ዘ​ፊ​ያ​ሽን ሠር​ተ​ዋል፤ መቅ​ደ​ስ​ሽ​ንም በዝ​ኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪ​ቲም ደሴ​ቶች ዛፍም ቤቶ​ች​ሽን ሠር​ተ​ዋል።


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


በግ​ብፅ ምድር በሚ​ግ​ዶ​ልና በጣ​ፍ​ናስ፥ በሜ​ም​ፎ​ስም፥ በፋ​ቱ​ራም ሀገር ስለ ተቀ​መጡ አይ​ሁድ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦


አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።


የዘ​ምሪ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የኤ​ላም ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የሜ​ዶን ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ይስጡ፤ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በደ​ሴ​ቶች ይና​ገሩ።


ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።


ከግ​ብ​ፅም በወጣ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ነበረ፥ በአ​ሦር ለቀ​ረው ለሕ​ዝቡ ጎዳና ይሆ​ናል።


ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ለወ​ጥ​መድ፥ ለፍ​ዳና ለዕ​ን​ቅ​ፋት ትሁ​ን​ባ​ቸው፤


በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።


ያመ​ለ​ጠው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።


የግ​ብ​ፅ​ንም ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ወደ ተወ​ለ​ዱ​ባ​ትም ምድር ወደ ጳት​ሮስ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ያም የተ​ዋ​ረ​ደች መን​ግ​ሥት ይሆ​ናሉ።


“ኤላ​ምም በዚያ አለች፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ ሳይ​ገ​ረ​ዙም ወደ ታች​ኛው ምድር ወር​ደ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ተ​ዋል።


ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ ትፈ​ለ​ጋ​ለህ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ በነ​በሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰ​በ​ሰ​በች፥ ከሰ​ይፍ ወደ ተመ​ለ​ሰች ምድር ትገ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ከሕ​ዝብ ውስጥ ወጥ​ታ​ለች፤ ሁሉም በሰ​ላም ይቀ​መ​ጡ​በ​ታል።


በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤


እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ኀይ​ልህ፥ በጸ​ና​ውና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ውም ክን​ድህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ።


ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።


የኤ​ላ​ምም ሰዎች አፎ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ከሙ፤ በፈ​ረስ የተ​ቀ​መ​ጡና አር​በ​ኞች ሰዎች፥ የአ​ር​በ​ኞ​ችም ሠራ​ዊት ነበሩ።


እነሆ፥ እነ​ዚህ ከሩቅ፥ እነ​ሆም፥ እነ​ዚህ ከሰ​ሜ​ንና ከም​ዕ​ራብ፥ እነ​ዚ​ህም ከፋ​ርስ ሀገር ይመ​ጣሉ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios