Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለኢ​ዮ​አ​ካ​ዝም ከኀ​ምሳ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ከዐ​ሥ​ርም ሰረ​ገ​ሎች፥ ከዐ​ሥር ሺህም እግ​ረ​ኞች በቀር ሕዝብ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም፤ የሶ​ርያ ንጉሥ አጥ​ፍ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ በአ​ው​ድ​ማም እን​ዳለ ዕብቅ አድ​ቅ​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከኢዮአካዝ ሰራዊት የተረፈው ዐምሳ ፈረሰኞች፣ ዐሥር ሠረገሎችና ዐሥር ሺሕ እግረኛ ወታደር ብቻ ነው፤ ይህ የሆነበትም ምክንያት የሶርያ ንጉሥ የቀረውን ስለ አጠፋውና እንደ ዐውድማ ብናኝ ስለ አደረገው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኃይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኀይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለኢዮአካዝም ከአምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥርም ሠረገሎች፥ ከዐሥር ሺህም እግረኞች በቀር ሕዝብ አልቀረለትም፤ የሶርያ ንጉሥ አጥፍቶአቸዋልና፤ በአውድማም እንዳለ ዕብቅ አድቅቆአቸዋልና።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 13:7
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች በብ​ረት መጋዝ ሰን​ጥ​ቀ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደ​ማ​ስቆ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ።


ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።


አሁን እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተስ​ማማ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።


አክ​ዓ​ብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ደነ​ገጠ፤ ልብ​ሱ​ንም ቀደደ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰም ሄደ፤ በሰ​ው​ነ​ቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡ​ቴ​ንም በገ​ደ​ለ​በት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።


ኤል​ዛ​ቤ​ልም በሰ​ማች ጊዜ አክ​ዓ​ብን፥ “ናቡቴ ሞቶ​አል እንጂ በሕ​ይ​ወት አይ​ደ​ለ​ምና በገ​ን​ዘብ ይሰ​ጥህ ዘንድ እንቢ ያለ​ውን የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ ተነ​ሥ​ተህ ውረስ” አለ​ችው።


ሳሙ​ኤ​ልም ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሊገ​ናኙ ሄዱ። ከጌ​ል​ጌ​ላም ተነ​ሥ​ተው ወደ ብን​ያም ገባ​ዖን መጡ፤ ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድ​ስት መቶም የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨ​ኋ​ቸው፤ እንደ ጎዳ​ናም ጭቃ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደቀ​ደ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios