ዘፍጥረት 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄን፣ በመካከላቸው ከምኖር ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ጋራ እንዳታጋባው በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ማልልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤ |
አሁንም በእኔም፥ በልጄም፥ በወገኔም፥ ከእኔም ጋር ባለ ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን በእንግድነት መጥተህ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ፥ ለተቀምጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።”
ከአባቴ ቤት፥ ከተወለድሁባት ምድር ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፤ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፥ “እግዚአብሔር በጐበኛችሁ ጊዜ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማላቸው።
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
በእነዚያም ወራት ረዓይት በምድር ላይ ነበሩ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸውን ያስጠሩ ኀያላን ሰዎች ሆኑ።
ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ፥ “በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን የምድር ነገሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል ።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም ደግሞ አለ፥ “ለእግዚአብሔር ቤት ለመንግሥቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበበኛና ብልሃተኛ፥ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ፥ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን።
እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን።
እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ዕዝራም እንዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጥረሃል፤ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት ይህን ከተቀበለ፥ እርሱ ምንም አይክፈል።
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፤ አትመለስምም፤ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእግዚአብሔር ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።”
እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፥ ከይሁዳም የወጣችሁ፥ በእውነት ሳይሆን፥ በጽድቅም ሳይሆን እርሱን እየጠራችሁ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤
እንዲሁም በምድር ላይ የተባረኩ ይሆናሉ፤ እውነተኛውን አምላክ ያመሰግናሉና፥ በምድርም ላይ በእውነተኛው አምላክ ይምላሉና፤ የቀድሞውንም ጭንቀት ረስተዋልና፤ በልቡናቸውም አያስቡትምና።
እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ፥ ከሰማይም በታች ፈጽመው ይጥፉ ትሉአቸዋላችሁ።
በበዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ ፈጽመው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ።
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፤ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይበላት፦ እግዚአብሔር የተረገምሽ ያድርግሽ ጎንሽን ያረግፈው ዘንድ እግዚአብሔር ከሕዝብሽ መካከል ለይቶ ያጥፋሽ፤ ሆድሽን ይሰንጥቀው፤
ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሠረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወደደችውን ታግባ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ይሁን።
አሁንም፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ አደረግሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ በእውነት ምልክት ስጡኝ።
አባቱና እናቱም፥ “ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች፥ ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለችምን?” አሉት። ሶምሶንም አባቱን፥ “ለዐይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ” አለው።
ዳዊትም፥ “ወደ እነዚያ ሠራዊት ልትመራኝ ትወድዳለህን?” አለው፥ እርሱም፥ “እንዳትገድለኝ፥ ለጌታዬም እጅ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ፤ እኔም ወደ እነዚያ ሠራዊት እመራሃለሁ” አለው።