Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እናንተም፦ “ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ” ትሉአቸዋላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ጣዖቶች ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ መሆናቸውንና አንተ እግዚአብሔር ጣዖቶችን ሁሉ እንደምትደመስስ ንገራቸው” አልከኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 10:11
14 Referencias Cruzadas  

ተራ​ሮ​ችም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ እንደ ሰም ቀለጡ፥ ምድር ሁሉ ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ቀለ​ጠች።


በእጅ የተ​ሠሩ ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ ይሰ​ው​ራሉ፤


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፣ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሥራ​ቸው ከንቱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጐ​በ​ኛ​ቸው ጊዜ ይጠ​ፋሉ።


አገ​ጣ​ጥ​መው የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተ​ጐ​በኙ ጊዜም ይጠ​ፋሉ።


የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤


በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር።


እን​ግ​ዲህ እኔ ጽድ​ቄ​ንና የማ​ይ​ረ​ባ​ሽን የአ​ን​ቺን በደል እና​ገ​ራ​ለሁ።


በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ቤቶች እሳ​ትን ያነ​ድ​ዳል፤ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ማል፤ ይማ​ር​ካ​ቸ​ው​ማል፤ እረ​ኛም ልብ​ሱን እን​ደ​ሚ​ቀ​ምል እን​ዲሁ የግ​ብ​ፅን ሀገር ይቀ​ም​ላ​ታል፤ ከዚ​ያም በሰ​ላም ይወ​ጣል።


በግ​ብፅ ምድ​ርም ያለ​ውን የፀ​ሐይ ከተማ ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ይሰ​ብ​ራል፥ የግ​ብ​ፅ​ንም አማ​ል​ክት ቤቶች በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል።”


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣዖ​ቶ​ቹን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም ከሜ​ም​ፎስ እሽ​ራ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ያም በግ​ብፅ ምድር አለቃ አይ​ሆ​ንም፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ፍር​ሀ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios