Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ሳሙኤል 20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዮና​ታን ዳዊ​ትን እንደ ረዳው

1 ዳዊ​ትም ከአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ሸሸ፤ ወደ ዮና​ታ​ንም መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ በደ​ልሁ? ነፍ​ሴ​ንም ይሻት ዘንድ በአ​ባ​ትህ ፊት ጥፋ​ቴና ኀጢ​አቴ ምን​ድን ነው?”

2 ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ​ንስ ያር​ቀው፤ አት​ሞ​ትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስ​ቀ​ድሞ ለእኔ ሳይ​ገ​ልጥ ትል​ቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያ​ደ​ር​ግም፤ አባ​ቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰ​ው​ረ​ኛል? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም” አለው።

3 ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።

4 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ነፍ​ስህ ምን ትፈ​ል​ጋ​ለች? እኔስ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?” አለው።

5 ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በን​ጉ​ሥም አጠ​ገብ ለምሳ አል​ቀ​መ​ጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እን​ድ​ሸ​ሸግ አሰ​ና​ብ​ተኝ ።

6 አባ​ት​ህም ቢፈ​ል​ገኝ፦ ለዘ​መ​ዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓ​መት መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና ዳዊት ወደ ከተ​ማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽ​ንቶ ለም​ኖ​ኛል በለው።

7 እር​ሱም፦ መል​ካም ነው ቢል ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ሰላም ይሆ​ናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእ​ርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዕወቅ።

8 እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ከባ​ሪ​ያህ ጋር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ለባ​ሪ​ያህ ቸር​ነ​ትን አድ​ርግ፤ በደል ግን ቢገ​ኝ​ብኝ አንተ ግደ​ለኝ፤ ለምን ወደ አባ​ትህ ታደ​ር​ሰ​ኛ​ለህ?”

9 ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ ከአ​ንተ ይራቅ፤ ከአ​ባቴ ዘንድ ክፋት በላ​ይህ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ያወ​ቅሁ እንደ ሆነ በከ​ተማ ባት​ኖ​ርም እን​ኳን ወደ አንተ መጥቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው።

10 ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን፥ “አባ​ትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነ​ገ​ረህ እንደ ሆነ ማን ይነ​ግ​ረ​ኛል?” አለው።

11 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እን​ውጣ” አለው። ሁለ​ቱም ወደ ሜዳ ወጡ።

12 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባ​ቴን መር​ምሬ እነሆ፥ በዳ​ዊት ላይ መል​ካም ቢያ​ስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አል​ል​ክም፤ ይህም ምል​ክት ይሁ​ንህ፤

13 አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።

14 እኔም በሕ​ይ​ወት ሳለሁ ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ግ​ል​ኛ​ለህ፤

15 ብሞ​ትም ቸር​ነ​ት​ህን እስከ ዘለ​ዓ​ለም ከቤቴ አት​ተው፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ጠላ​ቶች ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ከም​ድር ፊት ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ የዮ​ና​ታን ስም በዳ​ዊት ቤት ይገ​ኛል።”

16 ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።

17 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን እንደ ነፍሱ ይወ​ድድ ነበ​ርና እንደ ገና ማለ​ለት።

18 ዮና​ታ​ንም አለው፥ “ነገ መባቻ ነው፤ መቀ​መ​ጫ​ህም ባዶ ሆኖ ይገ​ኛ​ልና ትታ​ሰ​ባ​ለህ።

19 ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ለ​ገህ ጊዜ ትመ​ጣና ነገሩ በተ​ደ​ረ​ገ​በት ቀን በተ​ሸ​ሸ​ግ​ህ​በት ስፍራ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ በኤ​ር​ገብ ድን​ጋ​ይም አጠ​ገብ ቈይ።

20 እኔም በዓ​ላማ ላይ እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ ብዬ ሦስት ፍላ​ጻ​ዎ​ችን ወደ ዓላ​ማው እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ።

21 እነ​ሆም፦ ሂድ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ፈልግ ብዬ ብላ​ቴ​ና​ውን እል​ካ​ለሁ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወደ​ዚህ ነው፤ ይዘ​ኸው ወደ እኔ ና ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ለአ​ንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለ​ብ​ህም።

22 ብላ​ቴ​ና​ውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ና​ብ​ቶ​ሃ​ልና መን​ገ​ድ​ህን ሂድ።

23 አን​ተና እኔም ስለ ተነ​ጋ​ገ​ር​ነው፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ምስ​ክር ነው።”

24 ዳዊ​ትም በሜ​ዳው ተሸ​ሸገ፤ መባ​ቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመ​ብ​ላት ተቀ​መጠ።

25 ንጉ​ሡም እንደ ቀድ​ሞው በግ​ንቡ አጠ​ገብ በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ቆመ፤ አቤ​ኔ​ርም በሳ​ኦል አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ የዳ​ዊ​ትም ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ።

26 ሳኦ​ልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆ​ናል፤ ምን​አ​ል​ባ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም ይሆ​ናል፤ በእ​ው​ነ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም” ብሎ አስ​ቦ​አ​ልና በዚያ ቀን ምንም አል​ተ​ና​ገ​ረም።

27 ከመ​ባ​ቻም በኋላ በማ​ግ​ሥቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን የዳ​ዊት ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ፤ ሳኦ​ልም ልጁን ዮና​ታ​ንን፥ “የእ​ሴይ ልጅ ትና​ትና ዛሬ ወደ ግብር ያል​መጣ ስለ​ምን ነው?” አለው።

28 ዮና​ታ​ንም ለሳ​ኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተ​ማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግ​ሮኝ ተሰ​ና​ብ​ቶ​ኛል።

29 እር​ሱም፥ “ዘመ​ዶቼ በከ​ተማ ውስጥ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና፥ ወን​ድ​ሞቼም ጠር​ተ​ው​ኛ​ልና እባ​ክህ! አሰ​ና​ብ​ተኝ፤ አሁ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ልሂ​ድና ወን​ድ​ሞ​ቼን ልይ አለ፤ ስለ​ዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አል​መ​ጣም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

30 ሳኦ​ልም በዮ​ና​ታን ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “አንተ የከ​ዳ​ተ​ኞች ሴቶች ልጅ! የእ​ሴ​ይን ልጅ ለአ​ንተ ማፈ​ርያ፥ ለእ​ና​ት​ህም ኀፍ​ረተ ሥጋ ማፈ​ርያ እንደ መረ​ጥህ እኔ አላ​ው​ቅ​ምን?

31 የእ​ሴይ ልጅ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ መን​ግ​ሥ​ትህ አት​ጸ​ናም፤ አሁ​ንም ሞት የሚ​ገ​ባው ነውና ያን ብላ​ቴና ያመ​ጡት ዘንድ ላክ” አለው።

32 ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል፥ “ስለ ምን ይሞ​ታል? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

33 ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ።

34 አባቱ በእ​ርሱ ላይ ክፉ ነገ​ርን ሊያ​ደ​ርግ ስለ ቈረጠ ዮና​ታን ስለ ዳዊት አዝ​ኖ​አ​ልና እጅግ ተቈ​ጥቶ ከማ​ዕዱ ተነሣ፤ በመ​ባ​ቻ​ውም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ግብር አል​በ​ላም።

35 እን​ዲ​ህም ሆነ በነ​ጋው ዮና​ታን ከዳ​ዊት ጋር ምል​ክት ለማ​ድ​ረግ ወደ ተቃ​ጠ​ረ​በት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ታናሽ ብላ​ቴና ነበረ።

36 ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ሮጠህ የም​ወ​ረ​ው​ራ​ቸ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች ፈል​ግ​ልኝ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም በሮጠ ጊዜ ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ማዶ አሳ​ልፎ ወረ​ወ​ረው።

37 ብላ​ቴ​ና​ውም ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ወረ​ወ​ረ​በት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮና​ታን፥ “ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ።

38 ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ።

39 ዮና​ታ​ንና ዳዊት ብቻ ነገ​ሩን ያውቁ ነበር እንጂ ብላ​ቴ​ናው ምንም አያ​ው​ቅም ነበር።

40 ዮና​ታ​ንም መሣ​ሪ​ያ​ውን ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጥቶ፥ “ሂድ ወደ ከተማ ግባ” አለው።

41 ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ።

42 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos