1 ተሰሎንቄ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም። |
በዚያም ቀን በዚች ደሴት የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ለርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ ከአሦር ንጉሥ ራሳቸውን ያላዳኑ እኛን እንዴት ያድኑናል?” ይላሉ።
ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆንባችኋል።
ስለዚህ ምክንያት ጥፋት ይመጣብሻል፤ ጥልቀቱን አታውቂም፤ በውስጡም ትወድቂያለሽ፤ ጕስቁልና ይመጣብሻል፤ ማምለጥም አይቻልሽም፤ ሞት ድንገት ይመጣብሻል፤ አታውቂምም።
አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች በድንገት ይመጡብሻል፤ የወላድ መካንነትና መበለትነት ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ስለ ምን ተስፋ አደረግን? ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም፤ የፈውስን ጊዜ ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ድንጋጤ ሆነ።
አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ!
እንደምታምጥ፥ የበኵር ልጅዋንም እንደምትወልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸትሽን ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ሰለለ፤ እጆችዋንም ትዘረጋለች፤ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።
ሰላም ሳይኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፤ አንዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነርሱ ያለገለባ ይመርጉታል፤ ይወድቃልም፤
ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ልጅዋን ከወለደች በኋላ ስለ ደስታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥዋን አታስበውም፤ በዓለም ወንድ ልጅን ወልዳለችና።
‘እነሆ፥ እናንተ የምታቃልሉ፥ እዩ፤ ተደነቁም፤ ያለዚያ ግን ትጠፋላችሁ፤ ማንም ቢነግራችሁ የማታምኑትን ሥራ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”
“የዚህንም ርግማን ቃሎች በሰማችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስንፍና በማድረግ ሄጃለሁና ይቅር ይለኛል’ የሚል ቢኖር የበደለኛ ፍዳ ካልበደለ ጋር እንዳይተካከል፥
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበረና የሰሙትም ለእኛ አጸኑት።
ጌዴዎንም በድንኳን የሚኖሩ ሰዎች ባሉበት መንገድ በኖቤትና በዮግቤል በምሥራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራዊቱም ተዘልሎ ሳለ አጠፋቸው።