Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሆሴዕ 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ

1 ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።

2 ዳግ​መ​ኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚ​ሠ​ራው አም​ሳል ከወ​ር​ቃ​ቸ​ውና ከብ​ራ​ቸው ጣዖ​ትን ሠሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አል​ቋል።”

3 ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።

4 ሰማ​ይን ያጸ​ናሁ፥ ምድ​ር​ንም የፈ​ጠ​ርሁ፥ እጆ​ችም የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትን ያቆሙ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። እን​ዳ​ት​ከ​ተ​ላ​ቸ​ውም እነ​ር​ሱን አላ​ሳ​የ​ሁ​ህም። ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ አት​ወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚ​ያ​ድ​ንህ የለ​ምና።

5 በም​ድረ በዳና በዞ​ር​ህ​በት ምድር ሁሉ ጠበ​ቅ​ሁህ።

6 ከተ​ሰ​ማ​ራ​ችሁ በኋላ ጠገ​ባ​ችሁ፤ በጠ​ገ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ልባ​ችሁ ታበየ፤ ስለ​ዚ​ህም ረሳ​ች​ሁኝ።

7 ስለ​ዚ​ህም ለይ​ሁዳ ቤት እንደ አን​በሳ፥ ለኤ​ፍ​ሬ​ምም እንደ ነብር ሆን​ሁ​ባ​ቸው።

8 በአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም መን​ገድ አጠ​ገብ እንደ ተራበ ድብ እገ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሥር እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም የዱር አን​በ​ሶች ይበ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት ይነ​ጣ​ጠ​ቋ​ቸ​ዋል።

9 እስ​ራ​ኤል ሆይ! በመ​ከ​ራህ ጊዜ ማን ይረ​ዳ​ሃል?

10 ንጉ​ሥህ ወዴት አለ? በየ​ከ​ተ​ማህ ሁሉ እስኪ ያድ​ንህ! ንጉ​ሥና አለቃ ስጠኝ የም​ት​ለኝ እስኪ እነ​ርሱ ይበ​ቀ​ሉ​ልህ?

11 በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።

12 የዐ​መ​ፅ​ህን ወን​ጀል ታገ​ሥ​ሁት፤ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ቱም ተከ​ማ​ች​ት​ዋል ።

13 ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።

14 ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።

15 ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ይለ​ያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋ​ስን ያመ​ጣል፤ ሥሩን ያደ​ር​ቃል፤ ምን​ጩ​ንም ያነ​ጥ​ፋል፤ ምድ​ርን ያደ​ር​ቃል፤ የተ​ወ​ደዱ ዕቃ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos