Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አንቺ በሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በዝ​ግባ ዛፍም ውስጥ የም​ታ​ለ​ቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያ​ዘሽ ጊዜ እን​ዴት ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አንቺ፣ ‘በሊባኖስ’ ውስጥ የምትኖሪ፣ መኖሪያሽን በዝግባ ዛፍ የሠራሽ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ መከራ በላይሽ ሲመጣ ጩኸትሽ እንዴት ይሆን!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕመም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታቃስቻለሽ!”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አሁንማ ከሊባኖስ መጥቶ በተሠራ የሊባኖስ እንጨት ውስጥ በሰላም ዐርፋችሁ ትኖራላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ወላድ ሴት የምጥ ጣዕር ሲይዛችሁ ምን ይበጃችሁ ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ!

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 22:23
18 Referencias Cruzadas  

ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት!


እንደ ንስር መጥ​ቀህ ብት​ወጣ፥ ቤት​ህም በከ​ዋ​ክ​ብት መካ​ከል ቢሆን፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ እጄ ከዚያ ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ ወደ ሰማ​ይም ቢወጡ ከዚያ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


በዓ​ለት ንቃ​ቃት ውስጥ የም​ት​ቀ​መጥ፥ የተ​ራ​ራ​ውን ከፍታ የም​ት​ይዝ ሆይ! ድፍ​ረ​ት​ህና የል​ብህ ኵራት አነ​ሣ​ሥ​ተ​ው​ሃል። ቤት​ህ​ንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታ​ደ​ርግ፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሞ​አብ የሚ​ኖሩ ከተ​ሞ​ችን ትተው በዓ​ለት ውስጥ ተቀ​መጡ፤ በገ​ደል አፋ​ፍም ቤቷን እን​ደ​ም​ት​ሠራ እንደ ርግብ ሆኑ።


እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድን​ጋ​ያማ ሸለቆ የም​ት​ቀ​መጥ ሆይ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እና​ን​ተም፦ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠን ወይም ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችን የሚ​ገባ ማን ነው? የም​ትሉ ሆይ! እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ዐም​ጸ​ዋ​ልና፥ ቅዱስ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ረስ​ተ​ዋ​ልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ልቅ​ሶና ጩኸ​ትም ተሰማ።


ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ማደ​ሪ​ያህ የጸ​ናች ናት፤ ጎጆ​ህም በአ​ንባ ላይ ተሠ​ር​ቶ​አል፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ፥ ረጅ​ምም ጽፍር ያለው፥ ላባ​ንም የተ​ሞላ፥ መልከ ዝን​ጉ​ር​ጉር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባ​ኖስ መጣ፤ የዝ​ግ​ባ​ንም ጫፍ ወሰደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios