Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 35:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከቤ​ትህ ጠል ይረ​ካሉ። ከደ​ስ​ታ​ህም ፈሳሽ ታጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ያልታሰበ ጥፋት ይምጣባቸው፤ የሰወሩት ወጥመድ ይያዛቸው፤ ይጠፉም ዘንድ ወደ ጕድጓዱ ይውደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥ የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው፥ በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ያላሰቡት ድንገተኛ ጥፋት ይድረስባቸው፤ የደበቁት ወጥመድ ይያዛቸው በቈፈሩትም ጒድጓድ ወድቀው ይጥፉ!

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:8
18 Referencias Cruzadas  

አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።


የባ​ሕ​ሩን ዓሣ አን​በሪ የሚ​ያ​ው​ከው እርሱ ነው የሞ​ገ​ድ​ዋ​ንም ድምፅ የሚ​ቃ​ወ​መው ማን ነው?


አሕ​ዛብ በሠ​ሩት በደ​ላ​ቸው ጠፉ፥ በዚ​ያ​ችም በሸ​ሸ​ጓት ወጥ​መድ እግ​ራ​ቸው ተጠ​መደ።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos