የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 11

ጰጠሎሜዎስ (6ኛው) እስክንድር ድል መታ፤ ዳግማዊ ዲሜጥሮስ ሞተ

1 የግብጽ ንጉሥ ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነ ሠራዊትና ብዙ የጦር መርከቦችን ጨምሮ የእስክንድርን መንግሥት በተንኮል በእራሱ መንግሥት ላይ ጨምሮ ለመያዝ ፈለገ፤

2 የሰላም መግለጫ በመስጠት ወደ ሦርያ ሄደ፤ የከተማዎቹ ሰዎች በሮቻቸውን ከፈቱለትና ሊቀበሉት ወጡ፤ ንጉሥ እስክንድር አማቹን እንዲቀበሉ ስላዘዘዛቸው ተቀበሉት።

3 ጰጠሎሜዮስ ወደ ከተማይቱ እንደ ገባ ወዲያውኑ ጠባቂ ወታደሮች በየከተማው አደረገ።

4 ወደ አዛጦን ለመድረስ በተቃረበ ጊዜ የዳጐን ቤት መቃጠሉን፥ አዛጦንና አካባቢዎችዋ መደምሰሳቸውን፥ ሬሳዎች በዚህም በዚያም መጣላቸውን፥ ንጉሡ በሚያልፍበት ቦታ ሰብስበውና ደራርበው አስቀምጠዋቸው ስለ ነበር በውጊያው ጊዜ ተቃጥለው የነበሩትን ሰዎች ቅሪቶቻቸውንም አሳዩት።

5 ለማስወቀስ ሲሉ ዮናታን ያደረገውን ገለጡለት፤ እርሱ ግን ዝም አለ፤

6 ዮናታን ንጉሡን በታላቅ ክብር ለመቀበል ወደ ኢዮጲ መጣ፤ ሰላምታ ተሰጣጡና በዚያ ቦታ አብረው አደሩ።

7 ዮናታን ኤለውጥሮስ እስከሚባለው ወንዝ ድረስ ንጉሡን ሸኝቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

8 ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ በበኩሉ በባሕሩ አጠገብ እስከምትገኘው ስለውቅያ ድረስ በባሕሩ ዳር ዳር የሚገኙትን ከተሞች ያዘ፤ በእስክንድርም የሚሸርበውን ሴራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አደረሰው።

9 ወደ ንጉሥ ዲሜጥሮስ ልጄን በሚስትነት እሰጥሃለሁ፤ በአባትህ መንግሥትም ላይ ትነግሣለሁ።

10 እርሱ እኔን ለመግደል ስለፈለገ ልጄን ለእርሱ መስጠቴ አሳዝኖኛል።

11 መንግሥቴን መውሰድ ይመኝ ነበር በማለት ወቀሰው።

12 ሴት ልጁን ከእስክንድር ወሰደና ለዲመትሪዮስ ሰጠ፤ ከእስክንድር ጋር የነበረውን ግንኙነት አቋረጠ፤ ጥላቸውም እየተባባሰ ሄደ።

13 ጰጠሎሜዮስ ወደ አንጾኪያ ገባና የእስያን ዘውድ ደፋ፤ በዚህ ዓይነት የግብጽንና የእስያን ዘውዶች ተቀዳጀ።

14 በዚያን ጊዜ ንጉሥ እስክንድር በኪልቂያ ይገኝ ነበር፤ምክንያቱም በአካባቢው ሰዎች አምጸውበት ነበር።

15 የተደረገውን በሰማ ጊዜ ከጰጠሎሜዮስ ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ጰጠሎሜዎስም ሽሽቶ ሄደ፤ ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ጰጠሎሜዎስም ከብዙ ሠራዊት ጋር ሆኖ ተንቀሳቀሰና ድል መታው።

16 እስክንድር ወደ አረብ አገር ሸሽቶ ሄደ፤ ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ አሸነፈው።

17 ዘብድኤል የሚባል አረባዊ ሰው ግን የእስክንድርን ራስ ቆርጦ ለጰጠሎሜዮስ ላከለት።

18 ከሦስት ቀን በኋላ ግን ጰጠሎሜዮስም ሞተ፤ በምሽጉ ውስጥ የነበሩ ወታደሮችም በነዋሪው ሕዝብ ተገደሉ።

19 2ኛው ዲሜጥሮስ በመቶ ስልሳ ሰባት ዓመተ ዓለም ነገሠ።

የዮናታንና ዲሜጥሮስ ግንኙነት መጀመር

20 በእነዚያ ቀኖች ዮናታን የኢየሩሳለምን ምሽግ ከብቦ ለመውጋት የይሁዳን አገረ ሰዎች ሰበሰበ፤ በዚያ ብዙ የጦር ተሸከርካሪ አዘጋጀ።

21 በዚያን ጊዜ ሃይማኖት የሌላቸውና ሕግን የሚያከብሩ፥ ሕዝባቸውን የሚጠሉ ሰዎች ሄደው ዮናታንን የኢየሩሳሌምን ምሽግ እንደሚወጋ ለንጉሡ ነገሩት።

22 ይህን በሰማ ጊዜ ዲሜጥሮስ ተቆጥቶ ወደ ጰጦሎማይዳ ሄደ፤ ዮናታን ምሽጉን ከመክበብ እንዲቆጠብና በጰጦሎማይዳ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር በፍጥነት እንዲመጣ ጸፈለት።

23 ይህን በሰማ ጊዜ ዮናታን ምሽጉን እንዲከቡ አዘዘ፤ አንዳንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና አንዳንድ ካህናትን መረጠ፤ እርሱ ራሱም በአደጋው ተጋፈጠ።

24 ብር፥ ወርቅ፥ ልብሶችንና ሌሎችም እጅ መንሻዎች በብዛት ይዞ ንጉሡ ወዳለበተ ወደ ጰጦሎማይዳ ሄደ፤ በንጉሡም ፊት ሞገስ አገኘ።

25 ከሕዝቡ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ሊከሱት ብዙ ሙከራ አደረጉ፤

26 ነገር ግነ ንጉሡ ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት ሁሉ አደረገለት፤ በወዳጆቹም ፊት ከፍ ከፍ አደረገው።

27 ሊቀ ካህነቱንና በፊት የነበረውን ክብር ሁሉ አጸናለት፤ ከመጀመሪያዎቹ ወዳጆቹ ጋር እንዲቆጠረም አደረገው።

28 ዮናታን ለንጉሡ ሦስት መቶ መክሊት ለመስጠት ቃል በመግባት የይሁዳን አገርና የሰማሪያ ሦስት አውራጃዎችን ከግብር ነጻ እንዲያወጣቸው ጠየቀው፤

29 ንጉሡ በዚህ ተስማምቶ እንዲህ ሲል ለዮናታን ጻፈለት፤

አይሁዶችን የሚጠቅም ደንብ ወጣ

30 “ንጉሡ ዲሜጥሮስ ለወንድሙ ለዮናታን፤ ለአይሁድ ሕዝብ ሰላምታ ያቀርባል፤

31 ለዘመዳችን ለላስቴን የጻፍነው ደብዳቤ እናንተ እንድታውቁት ግልባጩ ለእናንተ ተልኳል፤

32 ንጉሡ ዲሜጥሮስ ለአባቱ ለላስቴን ሰላምታ ያቀርባል።

33 ለእኛ ጥሩ አስተሳሰብ ላላቸው ወዳጆቻችን ለሆኑትና በእኛ ዘንድ በቅን መንፈስ ለሚመሩት አስተሳሰብ ላላቸው ወዳጆቻችን ለሆኑትና በእኛ ዘንድ በቅን መንፈስ ለሚመሩት ለአይሁድ ሕዝብ መልካም ነገርን ለማድረግ ወስነናል፤

34 የይሁዳ አገርና ሦስቱን አገርና በኢየሩሳሌም መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ሰዎች ጥቅም እንዲውሉ እነዚህ አውራጃዎች በአካባቢያቸው ከሚገኙ አገሮች ሁሉ ጋር ከሰማርያ ተነጥለዋል፤ ቀድሞ ንጉሥ በየዓመቱ ይቀበላቸው የነበሩት የመሬታቸውና የዛፎቻቸው ፍሬዎች ግብሮች ለእነርሱ ይሆናሉ፤

35 ከጨው ምድር በላይ ለእኛ ይሰጥ ከነበረው ዓሥራትና ከልዩ ልዩ ግብሮች እንዲሁም ከዘውድ ቀረጥ ከአሁን ጀምሮ ነጻ ይሆናሉ።

36 እነዚህ ስጦታዎች መቼም፥ የትም ደግሞ አይነሱም።

37 እንግዲህ እናንተ የዚህን ደብዳቤ ግልባጭ ለማድረግ ትጉ፥ በቅዱስ ተራራ ላይ በታወቀው ቦታ እንዲቀመጥ ለዮናታን ይሰጠው”።

የዳግማዊ ዲሜጥሮስ በዮናታን ወታደሮች ብርታት በአንጾኪያ ከሞት መትረፍ

38 ንጉሥ ዲሜጥሮስ በሥሩ ያለው አገር በሰላም የሚገኝ መሆኑንና ሥልጣኑን የሚቃወም ምንም አለመኖሩን በማየት ሠራዊቱን ሁሉ አሰናብቶ እያንዳንዳቸው ወደመጡበት እንዲሄዱ አደረገ፤ ከእርሱ ጋር የቀሩት ከአሕዛብ ደሴት የቀጠራቸው የውጭ አገር ወታደሮች ብቻ ነበሩ።

39 በዚህ ምክንያት ከአባቶቹ ጋር የነበረ አንድ ትሪፎን የተባለ ሰው ሠራዊቱ በጠቅላላ በዲሜጥሮስ ላይ ማጐረምረማቸውን በተገነዘበ ጊዜ የእስክንድርን ልጅ አንጥዮኩስን ወደ ሚያሳድገው ወደ ዓረባዊው ኤማልቄስ ሄደ።

40 በአባቱ ቦታ ላይ ልጁ እንዲነግሥ ለእርሱ ልጁን እንዲያስረክበው ወተወተው፤ ዲማጥሮስ የዘዘውን ሁሉ አብራራለት፤ ወታደሮቹም ምን ያህል እንደሚጠሉት ነገረው፤ እዚያ ብዙ ቀኖች ተቀመጠ።

41 ንጉሡ ዲሜጥሮስ ከኢየሩሳሌም ምሽግና ከሌሎችም ምሽጐች ወታደሮቹን እንዲያስወጣ የሚነግሩለትን ሰዎች ዮናታን ወደ ንጉሡ ላከ፤ ምክንያቱም ወታደሮቹ ሁልጊዜ ለእስራኤል ጋር በመዋጋት ላይ ነበሩ።

42 ዲሜጥሮስ እንዲህ ሲል መልስ ላከ፤ “ለአንተና ለሕዝብህ የማደርገው ይህን ብቻ ሳይሆን ጊዜ ሳገኝ አንተንና ሕዝብህን በክብር ከፍ አደርጋችኋለሁ።

43 ለጊዜው አሁን ከጐኔ ተሰልፈው የሚዋጉ ሰዎች በትልክልኝ ደግ ነው፤ ምክንያቱም ወታደሮቼ ሁሉ ከድተውኛል።”

44 ዮናታን በጀግንነት የሚዋጉ ሦስት ሺህ ወታደሮች ወደ አንጾኪያ ላከለት፤ ንጉሡም ስለ ደረሱለት ደስ አለው።

45 ቁጥራቸው አንድ መቶ ሃያ ሺህ የሚያህል የከተማ ሰዎች ንጉሡን ለመግደል ፈልገው በከተማው መሀል ተሰበሰቡ።

46 የከተማው ሰዎች መንገዶቹን በወረሩ ጊዜና ውጊያውም በተጀመረ ጊዜ ንጉሡ አምልጦ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገባ፥

47 ንጉሡ አይሁዳውያንን እንዲረዱት ጠራቸው፤ እነርሱ ሁሉ በአጠገቡ ተሰበሰቡ፤ በዚያ ቀን በከተማው ብዙ ሺ ሰው ገደሉ።

48 ብዙ ምርኮ ከሰበሰቡ በኋላ በዚያኑ ቀን ከተማውን በእሳት አጋዩ፤ ንጉሡንም ከሞት አወጡት።

49 አይሁዳውያን ከተማውን እነደፈለጉት መያዛቸውን ባዩ ጊዜ ሰዎቹ ተስፋ ቆርጠው ወደ ንጉሡ ጮሁ፤

50 “ቀኝ እጅህን ስጠን፤ አይሁዳውያን በእኛ ላይና በከተማው ላይ የሚያደርጉትን ውጊያ እንደያቆሙ አድርግልን” ሲሉ ለመኑት።

51 የጦር መሣሪያዎቻቸውን ጥለው ሰላም አደረጉ። አይሁዳውያን በንጉሡና በመንግሥቱ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ሁሉ ፊት ብዙ ክብር አገኙ። በዚህ ዓይነት ዝና አትርፈው አይሁዳውያን ብዙ ምርኮ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

52 ንጉሥ ደሜጥሮስ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ሀገሩም በእርሱ አመራር ሥር በሰላም ኖረ።

53 ለዮናታን የገባለትን ቃል ሁሉ አጠፈ፤ ዮናታን ስላደረገለት በጎ ነገር ሁሉ ወሮታውን ካለመከፈሉም ባሻገር በየአቅጣጫው ያርቀው ጀመር።

የዮናታንና የዳግማዊ ዲሜጥሮስ ግጭት፤ የቤተሱር በስምዖን መያዝ፤ የአጾሩ አጋጣሚ

54 ከዚህ በኋላ ትሪፎን ተመልሶ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ገና በወጣትነቱ የነገሠውና ዘውድ የደፋው አንጥዮኩስ ነበር።

55 ዲሜጥሮስ ያሰናበታቸው ወታደሮቹ ሁሉ አንጥዮኩስ ዙሪያ ተሰበሰቡ፤ ዲሜጥሮስን ወጉትና ሸሹ፤ ድል ተመታ።

56 ትሪፎን ዝሆኖቹን ወሰደ፤ አንጾኪያንም ያዘ።

57 ወጣቱ አንጥዮኩስ ለዮናታን እንዲህ ሲል ጻፈለት “የሊቀ ካህናቱን ሹመት አጽንቼልሃለሁ፤ በአራቱ አውራጃዎች ላይ ሾሜሃለሁ፤ ቍጥር ህ ከንጉሥ ወዳጆች መካከል እንዲሆን አድርጌአለሁ”።

58 የወርቅ ዕቃዎችም ላከለት፤ በወርቅ ጽዋዎች እንዲጠጣ፥ ከፋይ እንዲለብስ፥ የወርቅ መቆለፊያም እንዲኖረው ሥልጣን ሰጠው።

59 ወንድሙን ሰምዖንን ከታየር መሰላሎች እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ አስተዳዳሪ እንዲሆን ሾመው።

60 ዮናታን መጥቶ ከኤፍራጥስ ከወንዝ ወዲያ ማዶ ያለውን አገርና ከተሞችን እየተዘዋወረ ተመለከተ፤ የሶሪያ አገር ወታደሮች በሙሉ ከእርሱ ጋር ሆነው ለመዋጋት አጠገቡ ተሰለፉ፤ ወደ አስቃሎን መጠ፤ የእዚያ ነዋሪዎች ሁሉ በታላቅ ክብር ተቀበሉት።

61 ከዚያ ወደ ጊዛ ሄደ፤ የከተማው ሕዝብ በሩን ዘጋበት፤ ከተማዋን ከበባት፤ ዙሪያዋንም በእሳት አጋየ፤ ዘረፉዋትም።

62 የገዛ ሰዎቹ ዮናታንን ለመኑት፤ እርሱም ቀኝ እጁን ዘረጋላቸው፤ ነገር ግን የሹማምንቶቻቸውን ልጆች በመያዣነት ያዘባቸውና ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው ከዚህ በኋላ እስከ ደማስቆ ድረስ እየተዘዋወረ ተመለከተ።

63 የዲመትሪዮስ የጦር መሪዎች ዲመትሪዮስን ከግዛቱ ሊያወርዱት ፈልገው በገሊላ በምትገኘው ቃዲስ አጠገብ ከብዙ ሠራዊት ጋር ሆነው መገኘታቸውን ዮናታን ሰማ።

64 ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት ወደ እነርሱ ሄደ፤ በሀገሩ ወንድሙን ስምዖንን ተወው፤

65 ስምዖንን ወደ ቤተሱር ሄዶ ሰፈረ፤ ዙሪያዋን ከቦና ዘግቶ ብዙ ቀኖች ተዋጋ፤

66 የእዚያ አገር ነዋሪዎች ሰላም ያደርግ ዘንድ ለመኑት፤ ተቀበላቸውም፤ ግን ከተማዋን አስለቀቃቸውና ከእዚያ አስወጣቸው፤ ቦታውን ያዘና እዚያው ወታደሮቹን ለጥበቃ መደበ፤

67 ዮናታንና ሠራዊቱ ግን በጌሣሬጥ ሐይቅ ዳር ላይ ሰፍረው ነበር፤ በማለዳ ተነሥተው ወደ ኀዞር ሜዳ ደረሰ።

68 መጀመሪያ በተራራው ላይ የግድያ ወጥመድ ካጠመዱ በኋላ ወራሪ ጦራቸውን በሜዳው ላይ እንዲወጋቸው ላኩበቸው።

69 ይህም የሆነው ዋናው የጦር ክፍላቸው በአይሁዳውያን ላይ ጥቃቱን በሚፈጽምበት ወቅት ነው።

70 የሠራዊቱ አለቆች የአቤሰሎም ልጅ ማታትያስን፥ የቃልፊ ልጅ ይሁዳ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ሲቀሩ ሌላ ማንም ሳይቀር የዮናታን ወታደሮች በሙሉ ሸሹ።

71 ዮናታን በኀዘን ልብሱን ቀደደና በራሱ ላይ አመድ ነስንሶ ጸለየ።

72 ከዚህ በኋላ ውጊያ ገጠሣቸው፤ አሸነፋቸውና ሸሹ።

73 ይህን ባዩ ጊዜ እነዚያ ሸሽተው የነበሩት ሰዎች እንደገና ከእርሱ ጋር ሆነው እስከ ቃዴስ ድረስ አባረሩዋቸው፤ የጠላት ሠፈር እስከሆነው ቃዴስም ድረስ አሳደዋቸው፤ ከእዚያው ሠፈሩ።

74 በዚያን ቀን ከውጭ አገር ሠራዊት ሦስት ሺህ ሰዎች ያህል ሞቱ። ዮናታንም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።