ኢሳይያስ 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፥ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። |
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ደማቸውም በኢዮአብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘለዓለም ይመለስ፤ ለዳዊት ግን ለዘሩና ለቤቱ፥ ለዙፋኑም የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም ይሁን።”
“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኀያል ጽኑዕና የተፈራኸው አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእኛና በነገሥታቶቻችን፥ በአለቆቻችንም፥ በካህናቶቻችንም፥ በነቢያቶቻችንም፥ በአባቶቻችንም፥ በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
ዙፋን በምሕረት ይጸናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ቤት ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፋጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል፤ ይፈርዳልም።
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክርን ከሚመክር በግብሩም ገናና ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል። እናንተ ግን ከንቱ መጽናናትን ታበዙ ዘንድ ትሻላችሁ።
ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይድናሉና፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንአት ይህን ያደርጋል።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
ነገራችን በፊቱ እንደ ሕፃን፥ በደረቅ መሬትም እንዳለ ሥር ሆነ፤ መልክና ውበት የለውም፤ እነሆ፥ አየነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ውበትም የለውም።
እርሱ ግን ስለ ኀጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ልጆቻቸውንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል፤ በጕልበታቸውም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሏቸዋል።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሰው ወደ ድኅነት ይመጣል።”
ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም።
አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
እነርሱም አባቶቻችን ናቸው፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።
ኀጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና፤ የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ፤ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን።
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።