Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ሳሙኤል 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዳዊት የእ​ግዝ!አብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እንደ አሰበ
( 1ዜ.መ. 17፥1-15 )

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያው ያሉ ጠላ​ቶ​ቹን ሁሉ ባወ​ረ​ሰው ጊዜ፥

2 ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።

3 ናታ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ ሂድና በል​ብህ ያሰ​ብ​ኸ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።

4 በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦

5 “ሂድ ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የም​ኖ​ር​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራ​ል​ኝም።

6 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ እሄ​ድና እመ​ላ​ለስ ነበር እንጂ በቤት አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ምና፥

7 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ጋር ባለ​ፍ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ፦ ስለ​ምን ቤትን ከዝ​ግባ እን​ጨት አል​ሠ​ራ​ች​ሁ​ል​ኝም? ብዬ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ይጠ​ብቅ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ላዘ​ዝ​ሁት ለአ​ንዱ በውኑ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁን?

8 አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤

9 በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆቹ ስም ስም​ህን ታላቅ አደ​ረ​ግሁ።

10 ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ብቻ​ቸ​ውን ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩት የለም፤ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የኀ​ጢ​አት ልጅ መከራ አያ​ጸ​ና​ባ​ቸ​ውም።

11 በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።

12 ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።

13 እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።

14 እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤

15 ከፊ​ቴም ከጣ​ል​ሁት ከሳ​ኦል ቤት እን​ዳ​ራ​ቅሁ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።

16 ቤቱ የታ​መነ ይሆ​ናል፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በፊቴ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።”

17 እን​ደ​ዚህ ቃል ሁሉ፥ እን​ደ​ዚ​ህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳ​ዊት እን​ዲሁ ነገ​ረው።


የዳ​ዊት የም​ስ​ጋና ጸሎት
( 1ዜ.መ. 17፥16-27 )

18 ንጉሡ ዳዊ​ትም ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?

19 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እኔ በፊ​ትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪ​ያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።

20 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ባሪ​ያ​ህን ታው​ቃ​ለ​ህና ዳዊ​ትስ ይና​ገ​ርህ ዘንድ የሚ​ጨ​ም​ረው ምን​ድን ነው?

21 ለባ​ሪ​ያ​ህም ታስ​ታ​ው​ቀው ዘንድ ስለ ቃልህ ምክ​ን​ያ​ትና እንደ ልብህ አሳብ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ አደ​ረ​ግህ።

22 ስለ​ዚ​ህም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ የለ​ምና፥ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአ​ንተ በቀር አም​ላክ የለ​ምና አንተ ታላቅ ነህ።

23 ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?

24 ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝብ አድ​ር​ገህ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ኸ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ አም​ላክ ሆነ​ሃ​ቸ​ዋል።

25 አቤቱ ሁሉን የም​ት​ገዛ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አሁ​ንም ለባ​ሪ​ያ​ህና ለቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ናው፤ አሁ​ንም እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ርግ።

26 ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታላቅ ይሁን።

27 አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሰ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ የባ​ሪ​ያ​ህን ጆሮ ከፈ​ትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ አልህ፤ ስለ​ዚ​ህም ባሪ​ያህ ይህ​ችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።

28 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አሁ​ንም አንተ አም​ላክ ነህ፤ ቃል​ህም እው​ነት ነው፤ ይህ​ንም መል​ካም ነገር ለባ​ሪ​ያህ ተና​ግ​ረ​ሃል።

29 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና አሁን እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊ​ትህ ይሆን ዘንድ የባ​ሪ​ያ​ህን ቤት እባ​ክህ ባርክ፤ በበ​ረ​ከ​ት​ህም የባ​ሪ​ያህ ቤት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos