Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 37:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅሬታ ከጽ​ዮ​ንም ተራራ ያመ​ለ​ጡት ይድ​ና​ሉና፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​አት ይህን ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ቅሬታ የሆኑት ከኢየሩሳሌም፣ የተረፉትም ከጽዮን ተራራ ይመጣሉና፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፥ ከጽዮን ተራራ ያመለጡት ይመጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህ ሁሉ እንዲፈጸም የሠራዊት አምላክ ቅናት ስለ ወሰነ ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ኰረብታ ከጥፋት የሚተርፉ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጥሉና፥ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 37:32
13 Referencias Cruzadas  

ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅሬታ፥ ከጽ​ዮ​ንም ተራራ የዳነ ይወ​ጣ​ልና፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​አት ይህን ያደ​ር​ጋል።”


ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ ስበክ እንዲህም በል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት።


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።


በዚ​ያም ጊዜ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅሬታ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት የዳ​ኑት ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በአ​ቈ​ሰ​ሉ​አ​ቸው ላይ አይ​ደ​ገ​ፉም፤ ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በእ​ው​ነት ይደ​ገ​ፋሉ።


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ጣል፤ ኀይ​ለ​ኛ​ው​ንም ያጠ​ፋል፤ ቅን​አ​ት​ንም ያስ​ነ​ሣል፤ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ በኀ​ይል ይጮ​ኻል።


ከሰ​ማይ ተመ​ለስ፤ ከቅ​ድ​ስ​ና​ህና ከክ​ብ​ርህ ማደ​ሪ​ያም ተመ​ል​ከት፤ ቅን​አ​ት​ህና ኀይ​ል​ህስ ወዴት ነው? የቸ​ር​ነ​ት​ህና የይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለ​ሃ​ልና።


ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios