Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 32:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እነሆ፥ ጻድቅ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ መሳ​ፍ​ን​ትም በፍ​ርድ ይገ​ዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እነሆ፥ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፥ መሳፍንትም በፍትህ ያስተዳድራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በጽድቅ የሚያስተዳድር ንጉሥ የሚነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ ሹማምንቱም በትክክል ይፈርዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እነሆ፥ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፥ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 32:1
24 Referencias Cruzadas  

ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


በዚ​ያም ዘመን በዚ​ያም ጊዜ ለዳ​ዊት የጽ​ድ​ቅን ቍጥ​ቋጥ አበ​ቅ​ል​ለ​ታ​ለሁ፤ እር​ሱም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን በም​ድር ያደ​ር​ጋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ተና​ገረ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጠባቂ በም​ሳሌ እን​ዲህ አለኝ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰ​ዎች መካ​ከል ተና​ገ​ርሁ፥”


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”


ኀጢ​አ​ትም ሞትን እንደ አነ​ገ​ሠ​ችው እን​ዲሁ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ጽድ​ቅን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ታነ​ግ​ሠ​ዋ​ለች።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።


“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


ለፍ​ር​ድና ከጥ​ፋት ለሚ​ያ​ድ​ና​ቸው ኀይል በፍ​ርድ መን​ፈስ ይቀ​ራሉ።


ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።


ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥


አም​ላ​ካ​ችን መጠ​ጊ​ያ​ች​ንና ኀይ​ላ​ችን ነው፤ ባገ​ኘን በታ​ላቅ መከ​ራም ጊዜ ረዳ​ታ​ችን ነው።


ከሙ​ቀት ለጥላ፥ ከዐ​ውሎ ነፋ​ስና ከዝ​ና​ብም ለመ​ጠ​ጊ​ያና ለመ​ሸ​ሸ​ጊያ ጎጆ ይሆ​ናል።


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


ዙፋን በም​ሕ​ረት ይጸ​ናል፥ በዚ​ያም ላይ በዳ​ዊት ቤት ፍር​ድን የሚሻ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ፋ​ጥን ፈራጅ በእ​ው​ነት ይቀ​መ​ጣል፤ ይፈ​ር​ዳ​ልም።


“እነሆ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰ​ጠ​ሁ​ትን መል​ካም የተ​ስፋ ቃል የም​ፈ​ጽ​ም​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይኖ​ራል፤ ጽዮ​ንም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ተሞ​ላች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios