Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነሆ፥ እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል በጽ​ዮን ተራራ ከሚ​ኖ​ረው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ነን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነሆ፤ እኔና ጌታ የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነሆ፥ ልጆቼና እኔ በጽዮን ተራራ ላይ ከሚኖረው ከሠራዊት አምላክ ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠን የማስጠንቀቂያ ምልክት ነን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 8:18
27 Referencias Cruzadas  

ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።


በዘ​መ​ኑም ጽድቅ ይበ​ቅ​ላል፥ ጨረ​ቃም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።


ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


በጽ​ዮን ለሚ​ኖር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ፤


እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል።


ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።


አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


ዳዊ​ትም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​አል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​መ​ጣል።


እና​ንተ ተሰ​ድ​ባ​ችሁ ነበር፤ መከ​ራም አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ችሁ ነበር፤ ተዘ​ባ​ብ​ተ​ው​ባ​ች​ሁም ነበር፤ በዚ​ህም መን​ገድ እን​ዲህ ከሆ​ኑት ጋር ተባ​ብ​ራ​ችሁ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢሳ​ይ​ያ​ስን አለው፥ “አን​ተና ልጅህ ያሱብ አካ​ዝን ትገ​ና​ኙት ዘንድ በል​ብስ አጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ወዳ​ለው ወደ ላይ​ኛው መታ​ጠ​ቢያ ቦታ ውጡ፤


ፊቴ​ንም በዚያ ሰው ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ጠ​ፋም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ወደ ነቢ​ዪ​ቱም ቀረ​ብሁ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስሙን ‘ቸኩ​ለህ ማርክ፤ ፈጥ​ነ​ህም በዝ​ብዝ’ ብለህ ጥራው።


ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።


በአ​ን​ተም በልጅ ልጅ​ህም ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለም​ል​ክ​ትና ለድ​ንቅ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።


“ቃሌም በላ​ያ​ችሁ ለክ​ፋት እን​ዲ​ጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እን​ደ​ም​ጐ​በ​ኛ​ችሁ ምል​ክ​ታ​ችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የብ​ረት ምጣ​ድም ወስ​ደህ በአ​ን​ተና በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ለብ​ረት ቅጥር አድ​ር​ገው፤ ፊት​ህ​ንም ወደ እር​ስዋ አቅና፤ የተ​ከ​በ​በ​ችም ትሆ​ና​ለች፤ አን​ተም ትከ​ብ​ባ​ታ​ለህ። ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናል።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።”


ደማ​ቸ​ውን የሚ​መ​ራ​መር እርሱ አስ​ቦ​አ​ልና፥ የድ​ሆ​ች​ንም ጩኸት አል​ረ​ሳ​ምና።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እረ​ኞቹ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸ​ውን አደ​ነቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios