Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 45:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ውኆ​ቻ​ቸው ጮኹ ደፈ​ረ​ሱም፥ ተራ​ሮ​ችም ከኀ​ይሉ የተ​ነሣ ተና​ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፥ ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በክብርና በግርማ የተሞላህ ኀያል ንጉሥ ሆይ፥ ሰይፍህን ታጠቅ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 45:3
22 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።


በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፤ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኀይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


አፌ​ንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድ​ር​ጎ​አል፤ በእጁ ጥላ ሰው​ሮ​ኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላ​ጻም አድ​ር​ጎ​ኛል፤ በሰ​ገ​ባው ውስ​ጥም ሸሽ​ጎ​ኛል።


ሰማ​ያት የእ​ር​ሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ክብ​ሩን አዩ።


ወደ አንተ ጮኹ፥ ዳኑም፥ አን​ተ​ንም አመኑ፥ አላ​ፈ​ሩም።


የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።


ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።


ከተ​ና​ገ​ር​ነ​ውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ዙፋን ቀኝ የተ​ቀ​መጠ እን​ዲህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት አለን።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።


የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ረዳቱ የሆነ፥ መታ​መ​ኛ​ውም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ ሰው ብፁዕ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ስሙ​ንም ጥሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ።


ቃሉን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላከ፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምን ነገ​ራ​ቸው፤ እር​ሱም የሁሉ ገዢ ነው።


ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት።


እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሌላ መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፦ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “እሳት ከሰ​ማይ ወደ​ቀች፥ በጎ​ች​ህ​ንም አቃ​ጠ​ለች፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ህ​ንም በላች፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


የሚ​ያ​ዩኝ ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፤ ራሳ​ቸ​ውን እየ​ነ​ቀ​ነቁ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላሉ፦


በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።


ጕን​ጮቹ ሽቱን የሚ​ያ​ፈ​ስሱ የሽቱ መደብ ናቸው። ከን​ፈ​ሮቹ እንደ አበ​ቦች ናቸው፥ የሚ​ፈ​ስስ ከር​ቤ​ንም ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios