ዘዳግም 4:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብጽ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁ እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ ነበርን? |
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ፤ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን?” አሉት።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም ግብፃውያን እንደ ሞቱ በባሕር ዳር አዩ።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣህ።
ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።
በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ በግብፅ ምድር እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ስለ እናንተ አብሮአችሁ ይዋጋል፤
ዐይኖችህ ያዩአቸውን እነዚህን ታላላቆች የከበሩትን ነገሮች ያደረገልህ እርሱ መመኪያችሁ ነው፤ እርሱም አምላክህ ነው።
ዛሬ ልጆቻችሁ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ተግሣጽ፥ ታላቅነቱንም፥ የጸናችም እጁን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ ያዩና ያወቁ እንዳይደሉ ዕወቁ።
እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”
በእስራኤል ሁሉ ፊት በታላቅ ተአምር ሁሉና በጸናች እጅ፥ በተዘረጋችም ክንድ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አልተነሣም።
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ዕለተ ሰንበትን ትጠብቃትና ትቀድሳት ዘንድ አዘዘህ።
አንተ ልጅህን በለው፦ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ነበርን፤ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ፥ በተዘረጋችም ክንድ ከዚያ አወጣን፤
አምላክህ እግዚአብሔር ዓይንህ እያየች፥ ታላቅ መቅሠፍትን፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ የጸናችውንም እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።
ወደ እግዚአብሔርም በጮሃችሁ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ደመናንና ጭጋግን አደረግሁ፤ ባሕሩንም መለስሁባቸው፤ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብፅ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።