Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 20:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድም​ፃ​ች​ንን ሰማ፤ መል​አ​ክ​ንም ልኮ ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ እነ​ሆም፥ በም​ድ​ርህ ዳርቻ ባለ​ችው ከተማ በቃ​ዴስ ተቀ​ም​ጠ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኛም ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እርሱም ጩኸታችንን ሰምቶ ከግብጽ የሚያወጣንን መልአክ ላከልን፤ እነሆ አሁን እኛ በግዛትህ ወሰን ላይ ባለችው በቃዴስ እንገኛለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 20:16
14 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠራ​ዊት ፊት ይሄድ የነ​በ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ሄደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ ከፊ​ታ​ቸው ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ቆመ፤


“በመ​ን​ገድ ይጠ​ብ​ቅህ ዘንድ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ል​ህም ስፍራ ያገ​ባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መል​አ​ኬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ።


መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል።


ደግሞ እኔ ግብ​ፃ​ው​ያን የገ​ዙ​አ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልቅሶ ሰማሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም አሰ​ብሁ።”


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


“በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ በመ​ን​ገ​ዱም እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ወደ እር​ሻና ወደ ወይን ቦታ አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድ​ህም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ እስ​ክ​ን​ወጣ ድረስ በን​ጉሥ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን።”


ከቃ​ዴ​ስም ተጕ​ዘው በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤


የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos