2 ሳሙኤል 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ከክፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፥ “እንግዲህ በቃህ፤ እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ የደረሰው ጕዳት እግዚአብሔርን ስላሳዘነው፣ ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ በሚዘጋጅበት ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ መቅጣት ያለውን ውሳኔ ለውጦ ይቀሥፋቸው የነበረውን መልአክ “በቃህ! አቁም!” አለው፤ በዚህም ጊዜ መልአኩ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን በዘረጋ ጊዜ እግዚአብሔር ስለ ክፉው ነገር አዘነ፥ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፦ እንግዲህ በቃህ፥ እጅህን መልስ አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ነበረ። |
በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ።
እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከደድሆ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ! እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ” ብሎ እንዲሞት ለመነ።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።
ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
ደሙም ባላችሁባቸው ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም አያለሁ፤ እናንተንም እሰውራችኋለሁ፤ እኔም የግብፅን ሀገር በመታሁ ጊዜ የጥፋት መቅሠፍት አይመጣባችሁም።
እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ በአየ ጊዜ እግዚአብሔር በሩን ያልፋል፤ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተወውም።
እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ የአምላክ ነጐድጓድ፥ በረዶውም፥ እሳቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለቅቃችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህ አትቀመጡም” አላቸው።
“መንፈስ ከእኔ ይወጣልና፥ የሁሉንም ነፍስ ፈጥሬአለሁና ለዘለዓለም አልቀስፋችሁም፤ ሁልጊዜም አልቈጣችሁም።
በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተዉምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።”
አደርግባችሁ ዘንድ ከአሰብሁት ክፉ ነገር ተመልሻለሁና በዚች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፥ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።
ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፣ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፣ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሴዎናውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።
በኢያቡስም አንጻር ገና ሳሉ ፀሐይዋ ተቈለቈለች፤ ብላቴናውም ጌታውን፥ “ና፤ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ እናቅና፤ በእርስዋም እንደር” አለው።
“ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ።” ሳሙኤልም አዘነ። ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።