Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ አይ​ሆ​ንም፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ። እግዚአብሔርም “ይህ አይፈጸምም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ “ይህ አይሆንም፥” ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔርም ራርቶላቸው “ይህ ያየኸው ነገር አይፈጸምም!” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፥ ይህ አይሆንም፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 7:3
16 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መል​አ​ክን ሰደደ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይቶ ከመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ይቅር አለ፤ የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ው​ንም መል​አክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅ​ህን መልስ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


በተ​ኵ​ላና በእ​ባብ ላይ ትጫ​ና​ለህ፤ አን​በ​ሳ​ው​ንና ዘን​ዶ​ውን ትረ​ግ​ጣ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ሊያ​ደ​ርግ ስላ​ሰ​በው ክፋት ይቅር አለ።


በውኑ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝቡ ሁሉ ገደ​ሉ​ትን? በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ሩ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ አል​ተ​ማ​ለ​ሉ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር አይ​ተ​ዉ​ምን? እኛም በነ​ፍ​ሳ​ችን ላይ ታላቅ ክፋት እና​ደ​ር​ጋ​ለን።”


አደ​ር​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከአ​ሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር ተመ​ል​ሻ​ለ​ሁና በዚች ምድር ብት​ቀ​መጡ እሠ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ች​ሁም፥ እተ​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ች​ሁም።


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


ልባ​ች​ሁን እንጂ ልብ​ሳ​ች​ሁን አት​ቅ​ደዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘ​ገየ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ፥ ለክ​ፋ​ትም የተ​ጸ​ጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመ​ለሱ።”


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ ደግሞ አይ​ሆ​ንም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳል፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይራ​ራል፤ በያ​ሉ​በት መሳ​ለ​ቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ ደከመ፥ በጠ​ላ​ትም እጅ እንደ ወደቁ አይ​ቶ​አ​ልና።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos