Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 135 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሃሌ ሉያ።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

2 የአ​ማ​ል​ክ​ትን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

3 የጌ​ቶ​ችን ጌታ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

4 እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

5 ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

6 ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

7 ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

8 ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

9 ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

10 ከበ​ኵ​ራ​ቸው ጋር ግብ​ፅን የገ​ደለ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

11 እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

12 በጸ​ናች እጅ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

13 የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

14 እስ​ራ​ኤ​ልን በመ​ካ​ከሉ ያሳ​ለፈ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

15 ፈር​ዖ​ን​ንና ሠራ​ዊ​ቱን በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

16 ሕዝ​ቡን በም​ድረ በዳ የመራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ከዓ​ለት ውኃን ያፈ​ለቀ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

17 ታላ​ላቅ ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

18 ጽኑ​ዓን ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

19 የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥

20 የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

21 ርስት ምድ​ራ​ቸ​ውን ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥ ለባ​ሪ​ያው ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ የሰጠ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛን በመ​ዋ​ረ​ዳ​ችን ዐስ​ቦ​ና​ልና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

23 ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ አድ​ኖ​ና​ልና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

24 ለሥጋ ሁሉ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

25 የሰ​ማ​ይን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos