Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ዜና መዋዕል 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሰሎ​ሞን ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሠራ
( 1ነገ. 6፥1-38 )

1 ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በተ​ገ​ለ​ጠ​በት በአ​ሞ​ሪያ ተራራ ዳዊት ባዘ​ጋ​ጀው ስፍራ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።

2 በነ​ገ​ሠም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር መሥ​ራት ጀመረ።

3 ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣ​ለው መሠ​ረት ይህ ነው፤ ርዝ​መ​ቱም በዱ​ሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ።

4 በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው።

5 ታላ​ቁ​ንም ቤት በዝ​ግባ እን​ጨት ከደ​ነው፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ የዘ​ን​ባ​ባና የሰ​ን​ሰ​ለት አም​ሳ​ልም ቀረ​ጸ​በት።

6 ቤቱ​ንም በከ​በ​ረና በተ​መ​ረጠ ዕንቍ፥ በወ​ር​ቅም አስ​ጌ​ጠው፤ ወር​ቁም የፋ​ሩ​ሔም ወርቅ ነበረ።

7 ቤቱ​ንም፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ መድ​ረ​ኮ​ቹ​ንም፥ ግን​ቦ​ቹ​ንም፥ ደጆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበጠ፤ በግ​ን​ቦ​ቹም ላይ ኪሩ​ቤ​ልን ቀረጸ።

8 ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑ​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድ​ስት መቶ መክ​ሊት በሚ​ያ​ህል በጥሩ ወር​ቅም ኪሩ​ቤ​ልን ለበ​ጣ​ቸው።

9 የም​ስ​ማ​ሮ​ቹም ሚዛን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አምሳ ሰቅል ወርቅ ነበረ። የደ​ር​ቡ​ንም ጓዳ​ዎች በወ​ርቅ ለበጠ።

10 በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ውስጥ ከእ​ን​ጨት ሥራ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።

11 የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ንዱ የኪ​ሩብ ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ ርዝ​መት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

12 የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ አንዱ ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የቤ​ቱ​ንም ግንብ ይነካ ነበር፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ የሌ​ላ​ው​ንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

13 የእ​ነ​ዚ​ህም ኪሩ​ቤል ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ቆመው ነበር፤ ፊቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ለ​ከቱ ነበር።

14 ከሰ​ማ​ያ​ዊ​ውም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊ​ውም፥ ከቀ​ዩም ሐር፥ ከጥ​ሩም በፍታ መጋ​ረ​ጃ​ውን ሠራ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም ጠለ​ፈ​በት።

15 በቤ​ቱም ፊት ቁመ​ታ​ቸው ሠላሳ አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች ሠራ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ላይ የነ​በ​ረው ጕል​ላት አም​ስት ክንድ ነበረ።

16 እንደ ድሪ ያሉ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ች​ንም ሠርቶ በአ​ዕ​ማዱ ራስ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ መቶም ሮማ​ኖች ሠርቶ በሰ​ን​ሰ​ለቱ ላይ አደ​ረ​ጋ​ቸው።

17 አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራ​ቸው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos