ኤርምያስ 26:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተዉምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 “ታዲያ፣ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉትን? ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን ፈርቶ ምሕረት አልለመነምን? እግዚአብሔርስ በእነርሱ ላይ ለማምጣት ያሰበውን ቅጣት አልተወምን? በራሳችን ላይ እኮ ታላቅ ጥፋት እያመጣን ነው።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ ንጉሡ ጌታን አልፈራን? ወደ ጌታስ አልተማጠነምን? ጌታስ በእነርሱ ላይ የተናገረውን ክፉ ነገር አልተወምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ታዲያ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሚክያስ እንዲገደል አደረጉን? አይደለም! ይልቁንም ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በመፍራት ምሕረት እንዲያደርግለት ተማጠነ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ዐቅዶት የነበረውን መቅሠፍት መለሰ፤ እኛ ግን አሁን አሠቃቂ የሆነ መቅሠፍት በራሳችን ላይ ለማምጣት ተዘጋጅተናል።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተውምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን። Ver Capítulo |