እኅቴ ነች ያለኝ ራሱ አብርሃም ነው፤ እርስዋም ወንድሜ ነው ብላኛለች፤ እኔ ይህን ያደረግኹት በቅንነትና በንጹሕ ኅሊና ስለ ሆነ ምንም በደል አልፈጸምኩም” አለ።
መዝሙር 7:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኅሊናንና ልብን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ! የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ የጻድቃንንም ደኅንነት ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥ አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣን ክፋት ያልቃል፥ ጻድቃንን ግን ታቃናቸዋለህ፤ እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል። |
እኅቴ ነች ያለኝ ራሱ አብርሃም ነው፤ እርስዋም ወንድሜ ነው ብላኛለች፤ እኔ ይህን ያደረግኹት በቅንነትና በንጹሕ ኅሊና ስለ ሆነ ምንም በደል አልፈጸምኩም” አለ።
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
እኔም እንዲህ በማለት ጸለይኩ፦ “የሠራዊት አምላክ ሆይ! የሰውን ልብና አእምሮ የምትመረምር አንተ ቅን ፈራጅ ነህ፤ እነሆ ችግሬን ለአንተ አስታወቅሁ፤ ስለዚህም በእነዚህ ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን በቀል እንዳይ አድርገኝ።”
የሠራዊት አምላክ ሆይ! ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤ የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤ አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤ ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ።
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”
እኔ በማበሥረው የምሥራች ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚተላለፈው መልእክትና ከጥንት ዘመን ጀምሮ ተደብቆ በቈየው፥ አሁን ግን በተገለጠው የእውነት ምሥጢር አማካይነት እርሱ በእምነታችሁ እንድትቆሙ ሊያደርጋችሁ ይችላል።
በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።