Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 35:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ጌታዬና አምላኬ ሆይ! ተነሥተህ ተከላከልልኝ፤ ተነሥተህም ፍረድልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ! ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አምላኬ ጌታዬም፥ ትፈርድልኝ ዘንድ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:23
14 Referencias Cruzadas  

ጌታ ሆይ! ንቃ! ስለምንስ ታንቀላፋለህ? ተነሥ! ለዘለዓለም አትተወን!


እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ ተነሥ፤ የጠላቶቼንም ቊጣ አስወግድ፤ ፍርድ እንዲስተካከል ባዘዝከው መሠረት እኔን ለመርዳት ተነሥ፤


ቶማስም “ጌታዬ! አምላኬም!” ሲል መለሰለት።


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።


እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።


እርሱም ‘አንተ አባቴና አምላኬ ነህ፤ አንተ አምባዬና አዳኜ ነህ’ ይለኛል።


ለኤፍሬም፥ ለብንያምና ለምናሴ ራስህን ግለጥ፤ ኀይልህን አነሣሥተህ መጥተህ አድነን።


ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤ ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።


ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ፤ ከላይም ሆነህ ንገሥ።


ኅሊናንና ልብን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ! የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ የጻድቃንንም ደኅንነት ጠብቅ።


መጨቈናችንንና ችግራችንን ቸል በማለት ስለምን ከእኛ ትሰወራለህ?


አምላክ ሆይ! ተነሥ! ስምህን የሚዳፈሩትን ተከላከል! እነዚህ ሞኞች ቀኑን ሙሉ በአንተ ላይ እንደሚሳለቁ ተመልከት።


ስለ መብቴ ተከራከርልኝ፤ አድነኝ፤ በተስፋ ቃልህም መሠረት በሕይወት አኑረኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! በእኔ ላይ የደረሰውን በደል ሁሉ አይተሃልና ፍትሕን ስጠኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios